የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በአሽባሪው የህውሃት ቡድን ለወደሙ ትምህርት ቤቶች የሚሆን የተማሪዎች መቀመጫ ወንበር ድጋፍ አደረገ ፡፡
______________________________________________________________
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በአሽባሪው የህውሃት ቡድን በደባርቅ ወረዳ ለወደሙ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች መቀመጫ ወንብር ድጋፍ አድርጓል ፡፡
የደባርቅ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት አጠቃላይ ትምህርት ምክትል ሃላፊ አቶ መላኩ አለምነው እንደተናገሩት የክልሉ ትምህርት ቤት በዞኑ ትምህርት መምርያ በኩል ሁለት መቶ ሰባ ወንበር ድጋፍ አደርጎል ፡፡
በወረዳው በአሽባሪው የህውሃት ቡድን ሃያ ሁለት ትምህርት ቤቶች ወንበራቸው ፣ጠረጴዛቸው ፣ሰሌዳቸው ፣መጽሃፍቶች እና የትምህርት ማስረጃዎች ወድሞባቸዋል ፡፡ በአጠቃላይ በእነዚህ ትምህርት ቤቶች 24‚833‚300 ( ሃያ ስምንት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ ሶስት መቶ) ብር የሚገመት ብር ወድሟል ብለዋል ፡፡
አቶ መላኩ አያይዘውም የክልሉ ትምህርት ቢሮ የጀመረው ድጋፍ ጥሩ ነው ፡፡ ትምህርት የሁሉም ነገር መሰረት መሆኑን በመረዳት እነዚህ በትግራይ ወራሪ ሃይል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን የተሟላ የመማር ማስተማር ስራቸውን ለማስጀምር መንግስትም ሆነ ባለሃብቶችና በጎ አድራጊዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘገባው የደባር ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau

By awoke

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *