አቶ በላይነህ ክንዴ የሚያስገነቡት ቤተ መጽሐፍት ግንባታ ከ50 በላይ ደረሰ
_____________________________________________________________
ባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ በፍኖተ ሠላም ከተማ በዳሞት መሠናዶ ትምህርት ቤት ዘመናዊ ቤተ መጽሐፍት ለማስገንባት ቃል ገብተው ነበር ።
በቃላቸው መሠረትም በባለፈው ግንቦት 2013 ዓመተ ምህረት የቤተመጽሐፍቱን ግንባታ አስጀምረዋል ። በአሁኑ ሰዓት ግንባታው ከ50 በመቶ በላይ መድረሱን የግንባታው ተቆጣጣሪ መሐንዲስ ተናግረዋል ።
ቀጣዮቹ ሁለት ወራትም ግንባታውን ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው ።
አዲስ የሚገነባው ቤተ መጽሐፍት በትምህርት ቤቱ አሁን ያለውን ቤተ መጽሐፍና የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጅ /ICT/ችግርና ጥበት ለማቃለል ከፍተኛ አስተዋጾኦ ያለው ነው ።
መረጃው የፍኖተ ሰላም ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau

By awoke

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *