የዘማች ቤተሰቦችን መንከባከብና መደገፍም ሆነ ለሰራዊቱ ደጀን ለመሆን የምናሳየው መተባበር የጠላትን ቅስም የሚሰብርና ጦርነቱን በድል አድራጊነት እንድንወጣ የሚያደርግ ወሳኝ ተግባር ነው፡፡ አቶ አብርሃም አያሌው የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ
በምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኙ 2532 የዘማች ቤተሰብ ተማሪዎች ከ2.28 ሚሊዬን ብር በሚበልጥ ወጭ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገላቸው፡፡
የዘማች ቤተሰቦችን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የመስጠትና ለጋሾችን የማመስገን ፕሮግራም በምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ አዘጋጅነት የእውቅና መስጫ ፕሮግራም በዛሬው እለት በደብረ ማርቆስ ከተማ ተካሄዷል፡፡
የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አያሌው እንደገለጹት አሸባሪው የህወሃት ቡድን ከጅምሩ አማራን በጠላትነት ፈርጆ ላለፉት 30 አመታት በቁጥር የማይገለጽ የሰው ልጅን ህይወት ቀጥፏል፤ በአማራ ላይ በፈጸመው የኢኮኖሚ አሻጥር ክልሉ ወደ ድህነት አረንቋ እንዲገባና ሌሎች አለም አቀፍ ወንጀሎችን መስራቱ አልበቃው ብሎ አማራን ለማጥፋት ኢትዬጵያን ለማፍረስ ወስኖ ወረራ ከፍቶብናል፡፡ ይህንን ወረራ ለመቀልበስ የመንግስትን ጥሪ የተቀበሉ የዞናችን ጀግኖች ማቄን ጨርቄን ሳይሉ ወረ ግንባር ዘምተው አሸባሪ ቡድኑን እየተፋለሙ ይገኛሉ፡፡ የእነዚህን ጀግና ቤተሰቦች ከትምህርት ገበታ እንዳይፈናቀሉ የትምህርት ቁሳቁስ ለመሟላት ድጋፍ ያድጋችሁና ድጋፍ ያስተባበራችሁ በጎፈቃደኛ ወጣቶች በዞኑ ህዝብና በዘማች ቤተሰቦች ስም ላመሰግን እወዳለሁ ብለዋል፡፡
የዘማች ቤተሰቦችንም ሆነ ግንባር ላይ የሚገኘውን ሰራዊት ደጀን ለመሆን የምናሳየው መተባበር የጠላትን ቅስም የሚሰብርና ጦርነቱን በድል አድራጊነት እንድንወጣ የሚያደርግ ወሳኝ ተግባር ነው ብለዋል፡፡ አቶ አብርሃም አያይዘውም የምስራቅ ጎጃም ህዝብ ለዘማች ቤተሰቦች ካደረገው ድጋፍ በተጨማሪ ክልሉ በከፈተው አካውንት 130 ሚሊዮን ብር በጥሬ ገንዘብ እንዲሁም ከ7 ጊዜ በላይ ሰንቅ ና ሰንጋዎችን ድጋፍ ማድረጉን አቶ አብርሃም ተናግረዋል፡፡
ትምህርት ላይ መስራት ሃገር እንድትቀጥል መሰራት መጣል በመሆኑ የዘማች ቤተሰቦችን በዘላቂነት በማገዝ፣ የትምህርት ተቋማትን የጎደላቸውን በመሟላት ሃላፊነት የሚሰማው ዜጋ የሚያፈሩ እንዲሆኑ ልናደርግ ይገባል ብለዋል፡፡
የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ስለሽ ተመስጌን እንደገለጽት ዞኑ የዘማች ቤተሰቦችን የትምህርት ቁሳቁስ ለማሟላት አቅዶ በሰራው ስራ ከ2.28 ሚሊዬን ብር በሚበልጥ ወጭ 2532 የዘማች ቤተሰብ ተማሪዎችን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል፡፡ አቶ ስለሽ አያይዘውም አቶ መቅደስ አክሊሉ የተባሉ ባለሃብትና ምሁር በ448 ሽ ብር 12 ሽ96 ደብተር፣ የተከበሩ ዶክተር ማስተዋል መኮነን በውጭ ሃገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዬጵያዊያን በማስተባበር በ93 ሽ ብር የትምህርት ቁሳቁስ፣ በማርዳ መልቲ ሚዲያና ፕሮሞሽና በደብረ ማርቆስ ከተማ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ወጣቶች 696ሽ 970 ብር የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ድጋፍ ያደረጉና ያስተባበሩ ሲሆን ወደ ዚህ ስራ እንድንገባ በማገዝ ወጣቶችን በማስተባበር የተከበሩ አቶ አሰማኸኝ አስረስ ያደረጉትን ድጋፍ በዞኑና በሚሊሻ ቤተሰቦች ስም ላመሰግን እወዳለሁ ብለዋል፡፡
አቶ ስለሽ አያይዘውም የትምህርት ስራ በመንግስት ብቻ እንደማይፈጸም የተገነዘቡ ኑሯቸውን በአሜሪካ ያደረጉት ወ/ሮ ሰናይት የ168 ሽ ብር በማሰባሰብ መላካቸውን፣ የኢትዬ ቴሌኮም ሰሜን ምእራብ ሪጅን 11280 ደብተር ለሁለት ወረዳዎች፣ በአሜሪካ የሚኖሩ ወንፈል በሚል የተደራጁ ሃገር ወዳዶች 44434 ለ2ኛ ደረጃ አጋዥ መጽሃፍ በ18 ሚሊዬን በብር፣ አቶ አብርሃም አይነት ሃገር ወዳዶች ትምህርት ቤት ለመስራት የሚያስችል ሃብት እንደተገኘ ተናግረዋል፡፡
የዞኑ አስተዳደር በጦርነቱ ትምህርት ቤታቸው ለመደመባቸውና ቤተሰባቸው ለሞቱባቸው 10ሽ ተማሪዎች የ1 አመት የትምህርት እድል ለመስጠት በወሰነው መሰረት እስካሁን 395 ተማሪዎች ብቻ ወደ ዞኑ መጥተው በመማር ላይ እንደሚገኙ አቶ ስለሽ ገልጸዋል፡፡
ለቀረበላቸው ጥያቄ 12ሽ96 ደብተር የሰጡት የአዲስ አበባው ነዋሪ አቶ መቅደስ አክሊሉ እንደገለጹት የዘማች ቤተቦችን የትምህርት ቁሳቁስ መስጠት ድጋፍ ሳይሆን ካግዴታችን በታች በመሆኑ ሌሎችንም በማስተባበር የዘማች ቤተሰቦችንም ሆነ ሰራዊቱን እንደግፋለን ብለዋል፡፡
በውጭ የሚኖሩ ተወላጆቸን በማስተባበር ድጋፍ ያደረጉት የተከበሩ ዶክተር ማስተዋል መኮነን ምእራባዊያን በሃገራችን ትምህርት ላይ እጅቸውን የሚያስረዝሙት፣ ሃገር በቀል እውቀት ይዞ በራሱ የማይተማመንና በአልባሌ ሁኔታ የሚባዝን ዜጋ እንዲፈራ ከመሻት በመሆኑ በወጣቱ ላይ የምናካሄደው ኢንቨስትመንት ትውልድ ተረካቢ ዜጋ ለማፍራት ሚናው የጎላ ነው ብለዋል፡፡
ትምህርት ሃገርን ከችግር የሚያወጣ አርቆ አሳቢ ትውልድ እንዲፈጠር የሚያደርግ እንዲሆን የሚያስችል በመሆኑ በራሱ የሚተማመን ሃገርን የሚያስቀድም ተቻችሎ መኖርን መርህ ያደረገ ዜጋ እንዲፈጠር ዘርፉ ጠንክሮ ሊሰራ ይገባል ያሉት ደግሞ የዘማች ቤተሰቦች እንዲረዱ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በማስተባበር ወደ ስራ ያስገቡት የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባል አቶ አሰማኸኝ አስረስ ናቸው፡፡
ድጋፍ ለመሰብሰብ ሲዟዟሩ የደብረ ማርቆስን ህዝብ ደግነት ያመሰገኑት በማርዳ መልቲ ሚዲያና ፕሮሞሽን አስተባባሪነት የተሳተፉት የደብረ ማርቆስ ከተማ በጎ ፈቃደኛ ወጣት ሁልጊዜ አሸብር ናቸው፡፡ እንደ ወጣቱ ገለጻ የዘማች ቤተሰቦችን ከዚህ በላይ ማገዝ እንፈልጋለን ምክንያቱም የእነሱ ቤተሰቦች ሃገር ለማዳን ቤተሰብ ትተው ታሪክ እየሰሩ በመሆኑ ብለዋል፡፡
በመድረኩ ድጋፍ ያደረጉ ግለሰቦች፣ ደጋፍ ያሰባሰቡ በጎ ፈቃደኞች፣የዘማች ቤተሰብ ተማሪዎች፣ የወላጅ ተወካዬች፣የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባላት በመድረኩ ላይ ተገኝተዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau

By awoke

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *