የትምህርት ሚኒስቴር የኦንላይን መማሪያ ስርዓትን እና ዲጂታል ላይብራሪ አገልግሎቶችን መስጠት ጀመረ
———————————-
ትምህርት ሚኒስቴር የመረጃ፣ የተግባቦትና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዲሁም የዲጂታል ቴክኖሎጂ አተገባበር ሥርዓትን ማሻሻል የሚያስችሉ መርሐ ግብሮችን ይፋ አድርጓል።
የኦንላይን መማሪያ ስርዓትን እና ዲጂታል ላይብራሪ አገልግሎቶቱ መደበኛና አጋዥ መጽሃፍት፣ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ትምህርት ሚኒስቴር ካዘጋጃቸው እና ለተማሪዎች ይጠቅማሉ ካላቸው ከተለያዩ የውጭ ምንጮች በማካተት ይዞ ቀርቧል::
አገልግሎቱ ለተማሪዎች ግብዓቶችን በክፍል፣ በትምህርት አይነት፣ በምዕራፍ በመምረጥ ለአጠቃቀም ቀላል ሆኖ ቀርቧል፡፡
በተጨማሪም የአካል ጉዳተኞችን እና ወደ ትምህርት ቤት መምጣት የማይችሉ ተማሪዎችን ችግር እንዲያቃልል ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን ልዪ ተሰጥኦ ያላችውን ተማሪዎች የትምህርት ስርዓቱን ሳይገደቡ መከታተል ያስችላልም ተብሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት ከሶስት ሺ በላይ የሚሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የመማር ማስተማር ግብዓቶብን በክፍል፣ በትምህርት አይነት እና በምዕራፍ ተከፋፍሎ ወደ ሲስተሙ የመጫን ስራ ተሰርቶ ግብዓቶቹን በነፃ በኢንተርኔት እና ከኢንተርኔት ውጪ በማውረድ መጠቀም ያስችላል፡፡
በቀጣይም ለመጀመሪያ ደረጃ እና የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች የዚሁ አግልግሎት ተጠቃሚ የማድረግ ስራ በፈጣን ሁኔታ እየተሰሩ መሆናችንን በደስታ እንገልጻለን፡፡
ተማሪዎችም የኦንላይን መማሪያ ስርዓትን እና ዲጂታል ላይብራሪ አገልግሎትን ለማግኘት የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል https://elearn.moe.gov.et
MOE

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *