“ሳይማር ያስተማረንን ማህበረሰብ ለማገዝ እና ለአንድ ሃገር እድገት እንዲሁም የለማ የሰው ሃይል ለመፍጠር ትምህርት የማይተካ ሚና አለው”
አቶ ደጀኔ ጥላሁን -የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳደሪ
ነሐሴ 14/2016(ትምህርት ቢሮ)
የደቡብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ “ ትምህርት ለትውልድ” በሚል መሪ ቃል የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል፡፡
የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ደስታ አስራቴ እንዳሉት በ2016 ዓ.ም በዞኑ ካሉ 1 ሽህ 80 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና 65 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 3 መቶ 52ቱ 1ኛ ደረጃ እና 21 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ 2ኛው ወሰተ ትምህርት ተማሪዎች ሲማሩ የቆዩ ቢሆንም ባጋጠመን የፀጥታ ችግር ምክንያት በእቅዳችን መሰረት ማስፈተን አልተቻለም ብለዋል፡፡
ስለሆነም የትምህርት ስራችን በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች እያጋጠሙት የትምህርት ስራችን ውጤታማ እንዳይሆን አድርጎታል በመሆኑም ችግሩን ለመቅረፈና ካለበት ስብራት ለመጠገን የሁሉም ባለድርሻ አካል ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመሬት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ እንዳሉት ባለፉት ዓመታት የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማትና ግንባታ እንደ ዞን ሰፊ እና ውጤታማ ስራ ሲሰራ የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ባሳለፍነው በሰሜኑ ጦርነትና አሁን ላይ በተፈጠረው የውስጥ የፀጥታ ችግር የትምህርት ተቋሙ በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቶል፡፡
ስለሆነም እንደ ሃገር የማክሮ ኢኮኖሚ ተግባራችንና የብልፅግና ስራችን ለማከናወን ትምህርት አስፈላጊ መሆኑ ታውቆ ተግባሩን ለትምህርት አመራር የሚተው ሳይሆን የሁላችንን ሰፊ እርብርብ እንደሚጠይቅ ገልፀው ።
የወደሙ እና ጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶች መልሶ ማቋቋም፣የትምህርት ቤት ቁሳቁሶችን ማሟላት፣ጥገና የሚያስፈልጋቸውን መጠገን ፣ከተማሪዎችና ቤተሰቦች ጋር ውይይት ማካሄድ ና በ2016 ዓ.ም ያልተማሩ ልጆች ለቀጣይ 2017 ዓ.ም ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ አመራሩና የትምህርት ቤተሰቦችን ሰፊ ጥረት ይጠይቃል ብለዋል፡፡
በመድረኩም የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ሪፖርት የቀረበ ሲሆን እንደ ዞን 3 መቶ 17 ትምህርት ቤቶች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከ38 ሚሊየን ብር በላይ መውደሙንም በሪፖርቱ ቀርቦል፡፡
የላይ ጋይንት የትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌትነት አሰፋ እንዳሉት በወረዳቸው የምዝገባ አፈፃፀሙ 86 በመቶ የነበር ቢሆንም በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት በ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 2 ሽህ 8 ተማሪዎች ማስፈተናቸውንና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 8 መቶ 31 ተማሪዎችን ማስፈተናቸውን ገልፀዋል ፡፡
አያይዘውም ለቀጣይ 2017 ዓ.ም ሰፊ እቅድ በማቀድ ወደ ስራ ለመግባት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋ ለዚህም የሃኖይማኖት አባቶችንስ ማህበረሰቡ ተግባሩን እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የእስቴ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አዱኛው ጉቤ እንዳሉት በ2016 ዓ.ም በተፈጠረው ወቅታዊ የፀጥታ ችግር በወረዳው የትምህርት ስራ ተቋርጦ የቆየ መሆኑን ገልፀው በ2017 ዓ.ም ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመስ እቅድ አቅደው እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ትምህርት ከማንኛውም የፖለቲካ ሁኔታ ነፃ መሆኑን ገልፀው በ1ኛ ደረጃ ከ40 ሽህ በላይ 2ኛ ደረጃ ከ13 ሽህ በላይ ተማሪዎችን ለማስተማር ማቀዳቸውን እና የተዘረፈውን ሀብትና ንብረት ከክረምት በጎ ፈቃደኞች ጋር በጋራ እየሰራን መሆኑንና የትምህርት ቤተሰቡና ማህበረሰቡ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት የየበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አስተላፈዋል፡፡
South Gondar Zone Communication
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
Boost this post

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *