በፀጥታ ችገር ሳቢያ የተዘጉ ት/ቤቶችን ለማስከፈት የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ እንደሆነ የአዊ ብሄ/አስ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።
“በትምህርት ነገን ዛሬ እንሰራ ” በሚል መሪ መልዕክት የአዊ ብሄ/አስ ትምህርት መምሪያ የ2017ዓ.ም የትምህርት ንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።
ነሐሴ 14 ቀን 2016(ትምህርት ቢሮ)
በንቅናቄ መድረኩ የመምሪያው ሀላፊ አቶ ደስታ አለሙ ፦ለነጋችንን የበለፀገች ሀገር ለመገንባት ዛሬ በምናስተምረው ትምህርት እንደሚወሰን ተናግረዋል ። ስለሆነም ትምህርት የቀጣይ ትውልድና ሀገር ግንባታ መሠረት የሚጣልበት ትልቅ ተቋም እንደሆነም ነው ያስገነዘቡት።
ባለፈው አመት በተከሰተው የፀጥታ ችግር በብሄረሰብ አስተዳደሩ በርካታ ት/ቤቶች መውደማቸውን የጠቀሱት ሀላፊው በዚህም በርካታ ህፃናት በትምህርት ገበታ ላይ እንዳይውሉ ተነፍገዋል። የተዘጉ ት/ቤቶችን ለማስከፈት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ ገልፀዋል።
ለቀጣዩ ትምህርት ዘመን ነሀሴ 20/2016 ዓ.ም ጀምሮ የተማሪ ምዝገባ እንደሚጀምር የተናገሩት አቶ ደስታ ለተግባራዊነቱ ሁሉም አካል መረባረብ ይገባል ነው ያሉት።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው ለተሳታፊ አካላት አቅጣጫ የሰጡት የአዊ ብሄ/ አስ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቴዎድሮስ እንዳለው፥ የፀጥታ መደፍረሱ የትውልዱን እውቀት ግብይት መጉዳቱን ገልፀዋል። በዚህም ሳቢያ በርካታ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ናቸው ብለዋል። የአዊ ህዝብ ለትምህርት እጅግ ቁርጠኛ የሆነ ማህበረሰብ መሆኑን የጠቆሙት ዋና አስተዳዳሪው ቀውስ ውስጥም ሆኖ ልጆቹን ለማስተማር ዋጋ ከፍሏል ነው ያሉት።
በቀጣይ ሳምንት ጀምሮ ት/ቤቶች ያሉባቸውን የግብዓት ክፍተቶች በመለየት የመማር ማስተማር ግብዓት ሟሟላት እንደሚገባ አሳስበዋል ። ከአሁኑ የሚመዘገቡ ተማሪዎችን በመለየት የተማሪ ምዝገባ በንቅናቄ መፈፀም እንዳለበትም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ትምህርት ለሀገር ግንባታ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ከወላጆች ፣ ከመምህራን እና ከአጋርና ባለድርሻዎች ጋር ስለ ትምህርት ጥራትና ተደራሽነት መግባባት መፍጠር እንደሚገባም ነው አቶ ቴዎድሮስ ያስገነዘቡት።
“ትውልድ ላይ መስራት ከግዴታዎች ሁሉ በላጭ ነው።” ያሉት አቶ ቴዎድሮስ የተማሪዎች የነፍስ ወከፍ በጀት ሁሉም ወረዳዎች በወቅቱ መመደብ እንደሚገባቸውም አቅጣጫ በመስጠት የዕለቱ የንቅናቄ መድረክ ተጠናቋል።
👉 መረጃው የአዊ ኮሙዩኒኬሽን ነው
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *