“ትምህርት ሰብዓዊ እና ሳይንሳዊ ማኅበረሰብ ለመገንባት የሚያስችል መሳሪያ ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
በአማራ ክልል በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሽልማት መርሐ ግብር ተካሂዷል።
በመርሃግብሩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) የበለፀጉ ሃገራት የዕድገታቸው ሚስጥር ትምህርት መሆኑን ተናግረዋል።
የነገዋ ኢትዮጵያ የዛሬ ተማሪዎችን ትመስላለች ያሉት ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) አያይዘውም ተማሪዎቻችን በአስቸጋሪ የክልላችን የፀጥታ ችግሮች ውስጥ አልፋችሁ ለዚህ ታላቅ ክብር ስለበቃችሁ ልትኮሩ ይገባል ብለዋል።
በመርሐ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በበኩላቸው ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ላደረጉ ሁሉ ምሥጋና አቅርበዋል።
ትምህርት ሰብዓዊ እና ሳይንሳዊ ማኅበረሰብ ለመገንባት የሚያስችል መሳሪያ መሆኑን የተናገሩት ርእሰ መሥተዳድሩ የሥነ ምግባር እና የሞራል ልዕልና ለመገንባት ትልቁ መሳሪያ ትምህርት መሆኑንም ገልጸዋል።
ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ አክለውም ትምህርት ቤቶች ከታለመላቸው ዓላማ ወጥተው የፖለቲካ ማስፈጸሚያ ሲሆኑ እንደሚታዩ ገልጸው በተለይም ባሳለፍነው የትምህርት ዘመን በአንዳንድ አካባቢዎች ትውልድን የሚያመክን እና ከፖለቲካ ነጻ የሆነ ትውልድ የሚቀረጽበት ተቋም መሆኑን የዘነጋ እንቅስቃሴዎች መታየታቸወን አስረድተዋል።
ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በመጨረሻም በዚህ ችግር ውስጥ ሆነውም ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
በመርሃግሩ ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ ክቡር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) የአብክመ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ አቶ ፈሰሃ ደሳለኝ በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ፣ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ተገኝተዋል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን Amhara Education Bureau

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *