************
በደሴ ዙሪያ ወረዳ በ029 ቀይ ገደል ቀበሌ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ከአልማ ከምግብ ዋስትና በተገኘ 8 ሚሊዮን ብር የተገነባው ባለ 4 ከፍል የመማሪ ህንፃን የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አሊ ይማም፣ የተለያ የደቡብ ወሎ ዞን እና የደሴ ዙሪያ ወረዳ አመራሮች በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ተገልጿል፡፡
በቀበሌው ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ሙሉጌታ ይመርና አርሶ አደር ሰብለ ማስረሻ እንዳሉት ቀደም ሲል እነሱ ከድናጋይና ከአቧራ ላይ ተቀምጠው ይማሩ እንደነበር አስታውሰው በቅርብ የተሻለ ደረጃ ያለው ትምህርት ቤት በአካባቢያቸው ባለመኖሩ ትምህርታቸውን ለመቋረጥ መገደዳቸውንም አስረድተዋል፡፡
አልማ ያስገነባላቸው ትምህርት ቤት ልጆቻቸው ጥራቱን በጠበቀ ትምህርት ቤት አንዲማሩ ስላደረገላቸው ደስተኛ መሆናቸውንና ለአልማ ያሚያደርጉትን ደጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስተያየት ሰጭዎቹ ገልፀዋል፡፡ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በቅርብ እንዲገነባላቸውም ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል፡፡
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል መሀመድ ማህበረሰቡ ለአልማ በሚያዋጣው ገንዘብ ከዚህ በፊትም ትምህርት ቤት፣ የጤና ተቋማት፣ የውሃ ተቋማት፣ መንገድና ለህብረተሰቡ የሚገለግሉ የጤናና የትምህርት ግብኣትን በማቅረብ ለወረዳው ልማት ትልቅ አሰተዋፅኦ ማድረጉን ገልፀዋል፡፡ አሁን ላይ ከአልማ በተገኘ 8 ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጎ የተገነባውን ትምህርት ቤት ወረዳው የግንባታ ቁሳቁሶችን በማቅረብና በወረዳው ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች በሙያቸው አንዲገነቡት በማድረግ ከስራ እድል ፈጠራ ጋር አቀናጅቶ በማሰራት ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አስገንዝበዋል፡፡
የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አለምነው አበራ እንዳሉት ዞኑ በእያንዳንዱ ወረዳዎች ሞዴል ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን የመገንባት አቅጣጫን በማስቀመጥ ሲወርድ ሲዋራድ የመጣውን የትምህርት ጥራት፣ በሽፋንና ተገቢነት ላይ የነበሩ ስትራቴጅክ የትምህርት ስብራት ባሻገር በወቅታዊ ችግሮች ምክንያት የመጣውን የትምህርት ስብራትም ለመጠገን ጥራታቸውን በጠበቁ ትምህርት ቤቶች ላይ ህፃናትን ከመጀመሪያው ጀምሮ ለማስተካከል አላማ አድርጎ የተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ እንዲህ አይነት ጥራታቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶችን ገንብቶ ማሳየት ከተቻለ ህብረተሰቡ ሌላ ተጨማሪ ትምህርት ቤት በመገንባት በኩል ያሳየው ተነሳሽነት በተግባር የታየ መሆኑን የገለፁት አቶ አለምነው አበራ የደሴ ዙሪያ ወረዳ 3 ሞዴል ትምህርት ቤቶችን በማስገንባት ከዞኑ ካሉ ወረዳዎች ግንባር ቀደም መሆኑን አስረድተዋል፡፡
Dessie City Administration Communication
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse