በዓለም የምግብ ፕሮገራም በጀት ከ114ሺ በላይ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለጸ፡፡
===============
ጥር 19/2017 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) የትምህርት ቤት ምገባ ለተማሪዎች የትምህርት አቀባበልና ውጤታማነት የጎላ ሚና እንዳለው አለማቀፋዊ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡
በክልላችንም በመንግስት፣በአጋር አካላት እና በማህበረሰቡ ተሳትፎ የትምህርት ቤት ምገባ እየተሰጠ ይገኛል፡፡ በተያዘው የትምህርተ ዘመን በዓለም የምግብ ፕሮገራም በጀት ብቻ በ5 ዞኖች ውስጥ በሚገኙ በ8 ወረዳዎች በ281 ትምህርት ቤቶች ከ114ሺ በላይ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸው ከክልሉ ትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
በፕሮጀክቱ የሚቀርቡ ምግቦች በፕሮቲን፣በካርቦሃይድሬት፣በቫይታሚንና ሚኒራልስ የበለጸጉ ናቸው ተብሏል፡፡ ምገባ መጀመሩ የተማሪዎችን ውጤት ከማሻሻል ባሻገር የተማሪዎችን የማቋረጥና የማሳለስ ምጣኔ አሻሽሏል፡፡
የምገባ አገልግሎቱ ከተጀመረ ወዲህ በተማሪዎችና ወላጆች የስራተ ምግብና የጤና ሁኔታቸው እየተሻሻለ መምጣቱም ተገልጿል፡፡
የዓለም የምግብ ፕሮገራም ለተማሪዎች ምግብ ከማቅረብ ባሻገር የምግብ ማብሰያ ማድቤት ግንባታ፣የምግብ ማብሰያና መመገቢያ ቁሳቁሶች እንዲሁም የንጽህና መጠበቂያ ሳሙና እና የትምህርት ቁሳቁሶችን በማሟላት አበረታች ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡ በርካታ ባለሙያዎችን በመቅጠር የስራ እድል በመፍጠርም ከፍተኛ አስተዋጾ እያደረገ ይገኛል፡፡
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
+4

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *