የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ወራት እቅድ አፈፃፀሙን በኮምቦልቻ ከተማ እየገመገመ ነው።
=============
ኮምቦልቻ_(ጥር 19/2017ዓ.ም)የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከደቡብ ወሎ፣ ደሴ ከተማ አስተዳደር፣ ኦሮሞ ብ/አስ/ዞን፣ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር፣ ዋግህምራ ብ/አስተዳደር፣ ሰሜን ወሎ እና ወልዲያ ከተማ አስተዳደር የትምህርት አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በኮምቦልቻ ከተማ እያካሄደ ነው።
በመድረኩ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ወንዶሰን ልሳነ ወርቅ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ለትምህርት ስራ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልፀው ከ75 ሚሊየን ብር በላይ በጀት መድበው ከ12204 በላይ ተማሪዎችን የምገባ መርሐ ግብር ተጠቃሚ እንዳደረጉ አብራርተዋል።
በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ቢሮ ም/ሃላፊ ወ/ሮ እየሩስ መንግስቱ እንደተናገሩት ሃገር በሰው ይገነባል ፤ ሠው ደግሞ በትምህርት ይታነፃል ብለዋል። ትምህርት የሰው ልጆች በጥልቀት እንዲያስቡና እንዲመራመሩ፣ ትናንትን እንዲተርኩ ፣ዛሬን እንዲኖሩ ነገን እንዲያልሙ የማድረግ መግነጢሳዊ ሃይል አለው ያሉት ም/ሃላፊዋ ትምህርት የሰው ልጆች የተግባቦት መጠናቸው እንዲሰፋ በር ይከፍታል። ሰዎች የሚፈልጉትንና የሚያስፈልጋቸውን በነፃ ፈቃዳቸው እንዲመርጡና እንዲወስኑ እድል ይሰጣል ብለዋል።
የክልሉ መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማምጣት በርካታ ስራዎች እየሰራ ቢሆንም የትምህርት ስራችን ያደሩናወቅታዊ ፈተናዎች ገጥመውታል ብለዋል። ለአብነትም ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች፣ በክልላችን በተፈጠረው የሰላም ችግር በ2017 ዓ.ም ብቻ 4.5 ሚሊየን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል። በችግሩም በርካታ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉና በከፊል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል። መምህራን ባስተማሩና ፊደል ባስቆጠሩ መክፈል የሌለባቸውን መስዋዕትነት ከፍለዋል ብለዋል።
ቀጥሎም የ2017ዓ.ም የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የአሐዳዊ ዋሽ ብሔራዊ ፕሮግራም ሪፖርት እና ተማሪዎችን ለማብቃት የሚሰሩ ስራዎች ሰነድ ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
+7

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *