የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ዳራ
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በአዋጅ ቁጥር 4/1988 ዓ.ም መቋቋሙ ይታወቃል፡፡ ይሁንና ቢሮዉ ስራ የጀመረዉ በ1985 ዓ.ም ነበር፡፡ በመሆኑም የቢሮዉን ስራዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እንዲቻል የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ተቋቋሟል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ከመምሪያ ወደ ሂደት ከዚያም ወደ ዳይሬክቶሬት አድጓል፡፡ እስከ አሁን ድረስም ቢሮንና መንግስትን የማገናኘት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡
አጠቃላይ አላማ
የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት የሚከተሉት አላማዎች አሉት
- የቢሮዉን እንቅስቃሴ የተመለከቱ መረጃዎችን ማጠናቀርና ማደራጀት
- የቢሮዉን እንቅስቃሴ ተመለከቱ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ
- ቢሮ ከደንበኞቹ ጋር ተገቢዉን መግባባት እንዲፈጥር መስራት
ግብ
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከደንበኞች ጋር አላማዉን ማሳካት የሚያስችለዉ መግባባት መፍጠር
ተግባርና ኃላፊነት
- መልካም አፈጻጸም ያላቸዉን መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የትምህርት አመራሮች፣ ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ መቀመር
- የቢሮዉን እንቅስቃሴ የተመለከቱ ሰነዶችን ከሚመለከታቸዉ አካላት ማሰባሰብና ማደራጀት
- መልካም ተሞክሮችን በበራሪ ወረቀት፣ በመጽሄትና በሌሎችም የህትመት ዉጤቶች በመሰነድ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ
- መልካም ተሞክሮዎችንና መፍትሄ የሚሹ ችግሮችን በመለየት በተለያዩ ሚዲያዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ
- የፎቶ ኤግዚቪሽን በማዘጋጀት ለህብረተሰቡ ማስጎብኘት
- ልዩ ልዩ ሁነቶችን በማዘጋጅት የተለዩ መልዕክቶችን ተደራሽ ማድረግ
- የጥናትና ምር ምር ስራዎችን በመስራት ቢሮዉ ከህብረተሰቡ ጋር ያለዉ ግንኙነት እንዲሻሻል ማድረግ
- የተለያዩ ክንዉኖችን የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ለህብረተቡ ማደረስ
- ዜናዎችን፣ ዶክመንታሪ ፊልሞችንና አጫጭር ማስታዎቂያዎችን መስራት
- ልዩ ልዩ በቢሮዉ የሚዘጋጁ መድረኮችን የታለማላቸዉን ግብ እንዲመቱ ማዘጋጀት
- ቢሮው እየሰጠ ስላለዉ አገልግሎት የህብረተሰቡን ስሜት ለማዎቅ የሚያስችሉ የዳሰሳ ጥናቶችን ማከናዎን
- የቢሮዉን ባለሙያዎች አገልጋይነት ሊያሳድጉ የሚችሉ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር ተግባቦቶችን ማሳደግ
- የቢሮዉን ከፍተኛ አመራሮች በልዩ ልዩ የትምህርት ጉዳዮች ላይ መግለጫ እንዲሰጡ ማድረግ