የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የስራ ርክክብ አደረጉ፡፡
——————————————–
በአዲሱ የመንግስት ምስረታ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከቀድሞ የትምህርት ሚኒስትር ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡
ለአዲሱ ሚኒስትርም የቀድሞ የትምህርት ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ) እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
በርክክቡ ወቅትም ለሚኒስትሩ ስለ ትምህርት ሚኒስቴር አደረጃጀትና እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች እንዲሁም ለወደፊት የታቀዱ እቅዶች በ ጌታሁን መኩሪያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
ፕሮፌሰር ብርሃኑ የትምህርት ሚኒስቴር ሀገሪቱ በርካታ ስራ ከምትጠብቅባቸው ዘርፎች አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ትውልድን ሊቀይር የሚችል ስራን ለመስራት የተቻለቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡
ካለው አመራርና ሰራተኛ ጋር በመወያየት ስራዎችን እንደሚሰሩም ሚኒስትሩ የገልፁ ሲሆን የሚኒስቴሩ አመራሮች ላደረጉላቸው አቀባበል አመስግነዋል፡፡
ዘገባው የትምህርት ሚኒስቴር ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau