College Teachers Education

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ የከፍተኛ ትምህርት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

የከፍተኛ ትምህርት ክትትል ዳይሬክቶሬት በአማራ ትምህርት ቢሮ ሥር ከተቋቋሙት ዒላማ ተኮር ዳይሬክቶሬቶች መካከል አንዱ ነው:: ዳሬክቶሬቱ የተቋቋመ በዋናነት በከልሉ ውስጥ የሚገኙ የመንግስት የመምህራን ትምህርት ተቋማትን በቅርብ ለመደገፍና ለመከታተል ሲሆን ዋና ተልዕኮውም በክልሉ ውስጥ የሚካሄደውን የመምህራን ትምህርትና ሥልጠና ጥራቱን ጠብቆ እንዲካሄድ መደገፍና ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠርና የመምህራን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ትምህርት ተኮር ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድና የማህበረሰብ አገልግሎት በመስጠት ለክልሉ ትምህርት እድገት የሚበረክቱትን አስተዋጾ ከፍ እንዲደርጉ ማገዝ ነው፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ክትትል ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለአብክመ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሲሆን በስሩ የዳይሬክቶሬቱን ዳይሬክተር ጨምሮ አራት ከፍተኛ ባለሙያዎችን በማስተባበር በቢሮው የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነቶችንይፈጽማል፡፡

በአማራብሔራዊክልላዊመንግስትትምህርትቢሮየከፍተኛትምህርትክትትልዳይሬክቶሬትዋናዋናተግባራትናሃላፊነቶች

 1. በክልሉ መንግስት የሚተዳደሩ የመምህራን ትምህርት ተቋማት የሚተዳደሩባቸውን ደንቦች፣ ስታንዳርዶችንና መመሪያዎች ማዘጋጀት፣
 2. የመጀመሪያ ደረጃ መምህራን ትምህርትና ስልጠና ሥርዓተ ትምህርት ክልላዊ ይዘት እንዲኖረው አድርጎ ማደራጀት፣ ማበልጸግና ትግበራውን መከታተል፣
 3. ከመምህራን ትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር ክልላዊ የመማሪያ ሞጁሎችና አጋዥ መጽሃፍትን ማዘጋጀትና ማሰራጨት፣
 4. የክልሉን ፍላጎት መሰረት በማድረግ አስፈላጊነታቸው የታመነባቸውን ልዩ ልዩ የስልጠና መርሃ ግበሮች መቅረጽ፣
 5. በመምህራን ትምህርት ኮሌጆች የአሰልጣኝ መምህራንን አቅም የሚገነቡ ተግባራትን በመፈጸምና በመከታተል የመምህራን ልማትን ውጤታማ ማድረግ፣
 6. የመምህራን ትምህርት ተቋማቱ በቁሳዊና ሰብአዊ ግብዓቶች የተሟሉ እንዲሆኑ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
 7. የክልሉን የመጀመሪያ ደረጃ መምህራን ፍላጎትንና የተቋማትን የማሰልጠን አቅም መሠረት በማድረግ የየዘመኑን ሠልጣኝ ዕጩ መምህራን ብዛት በመወሰን፣ ለየተቋማቱ ኮታ በመደልደልና የምልመላ መርሃ ግብር በማዘጋጀት ተማሪዎች ተመልምለው ትምህርት እንዲጀምሩ ማድረግ፣
 8. ከመምህራን ተቋማት ጋር በመተባበር ክልላዊ የዕጩ መምህራን የምልመላ ፈተና ማዘጋጀት፣
 9. የሱፕርቪዥን ድጋፍ በማካሄድና ገንቢ ግብረ መልስ በመስጠት ተቋማት ውጤታማ ትምህርትና ሥልጠና፣ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት እንዲያካሂዱ ማገዝ፣
 10. የኢንስፔክሽን ድጋፍ በማድረግ ተቋማት ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ መደገፍ፣
 11. በየወቅቱ የሚጋጥሙ ችግሮችን በማጥናት ቢሮው የተቋማትን ችግር የሚፈታበተን ሁኔታ ማመቻቸትና ለውሳኔ መነሻ የሚሆኑ ሃሳቦችን ማቅረብ፣
 12. የክልሉ መምህራን ተቋማት በትምህርት ዘርፍ የጥናትና ምርምር ማዕከላት እንዲሆኑ ሊያግዙ የሚችሉ ስልቶችን መቀየስና ተግባራዊ ማድረግ፣

More about Colleges contact Ato Lisanework

Phone:

Email: