Information Communication technology

የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጅ ዳይሬክቶሬት 

መግቢያ

በሀገራችን ትምህርት ለሁሉም ዜጋ በጥራት፣ በስፋት እና ወጥነት ባለው መልኩ ለማድረስ እንዲሁም ፍትሃዊነቱን ለማረጋገጥ እየተሰራ ሲሆን የአብክመ ትም/ቢሮም ኢን/ኮሙ/ቴክኖሎጂን ተግባራዊ በማድረግ የትምህርት ስርጫቱን ለማዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱን በማሻሻል መምህራንና ተማሪዎች ከልማዳዊ የመማር ማስተማር ሂደት በተጨማሪ ቴክኖሎጅውን በመጠቀም ዓለምአቀፋዊ እውቀቶችንና ልምዶችን በመቅሰም ያላቸውን እውቀት፣ ክህሎት፣ አመለካከት እና ልምድ እንዲያዳብሩ እንዲሁም የተሻለ ውጤት ሊያመጣ በሚችል መልኩ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡

ዓላማ

የኢን/ኮሙ/ቴክ/ዳይሬክቶሬት በክልል ትምህርት ቢሮ ስር በሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ፣ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤቶች እና የመምህራን ትም/ማሰልጠኛ ኮሌጆች የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂን ተግባራዊ በማድረግ የመማር ማስተማር ሂደቱ ዉጤታማ እንዲሆን ድጋፍ ማድረግ ነው፡፡

በዘርፉ የሚከናወኑ አበይት ተግባራት

  • በየደረጃው በሚገኙ የትምህርት ተቋማት የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት እንዲስፋፋ ማድረግ እና ተግባራዊነቱን መከታተል፡፡
  • በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት ተቋማት የቴክኖሎጂ አተገባበር ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን በጥናት በመለየት፡ ወቅታዊ መረጃን በማደራጀት መፍትሄ ይሰጣል ወይም የመፍትሄ አቅጣጫ ያቀርባል፡፡
  • መሰረታዊ የቴክኖሎጂ ግብዓት ችግር /የኮምፒዩተር፡ ኢንተርኔት፡…/ ያለባቸውን የትምህርት ተቋማት በመለየት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመስራት እንዲሟላላቸው ማድረግ፡፡
  • የተለያዩ መተግበሪያዎችን /ሶፍትዌሮችን/ በማልማት ወይም እንዲለሙ በማድረግ የመማር ማስተማር ሂደቱን ማሻሻል፡፡
  • የትምህርት ተቋማትን የመረጃ ልውውጥ፡ እና አያያዝ ስርዓትን ማዘመን
  • በየደረጃው ለሚገኙ የትምህርት ተቋም አመራሮች፡ ፈፃሚዎች፡ መምህራን ቴክኖሎጂውን በተገቢው እና በስራቸው ለዉጥ ሊያመጣ በሚችል መልኩ መጠቀም እንዲችሉ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ይሰጣል፡፡
  • ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንዲሁም አፈጻጸማቸውን በመገምገም ግበረ መልስ ይሰጣል፡፡
    ተ.ቁ ስም                                  የስራ ድርሻ አድራሻ
    ስ.ቁ ኢ.ሜ.ል
    1. አቶ ብርሀኑ በላይ ዳይሬክተር 0918804466 et.birr@gmaill.com
    2. አቶ ንጉሴ ዘሪሁን ባለሙያ 0918016789 Hasetnigussie1@gmail.com
    3. አቶ ሞላ ጌትነት ባለሙያ 0909138961 gytmgabtab@gmail.com
    4. አቶ ሞላ ሰንደቁ ባለሙያ 0918720284 molla057@gmail.com
    5. አቶ ተመስገን ጌታቸው ባለሙያ 0918726304 tomgetaye@gmail.com
    6. አቶ ድረስ ጤናው ባለሙያ 0923529702 yihalemtenaw@gmail.com
    7. ወ/ሮ ሀይማኖት ኃ/መስቀል ባለሙያ 0977975192 haymiyesami@gmail.com
    8. ወ/ሮ ትርንጎ ሽባባው ሴክሬታሪ 0932287484 Birukit2010@gmail com