Educational Input study and supply

                           በአብክመ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ግብአቶች ጥናትና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት

ተግባር፣ ሀላፊነት እና አደረጃጀት

መግቢያ

የትምህርትን አቅርቦትና ፍትሃዊ ስርጭት ለማሳካትና የተሻለ ደረጃ ለማድረስ ቀልጣፋ የሆነ የትምህርት ግብአት ጥናትና አቅርቦት የሥራ ሂደት መኖር የማይታበል ሃቅ ነው፡፡ በመሆኑም የትምህርት ግብአት ጥናትና አቅርቦት  ዋና የስራ ሂደት ቢሮው ብቁ ዜጋ የማፍራት ተልኮውን እውን ለማድረግ እንዲችል አጥንቶ ወደስራ ካስገባቸው  ዋና የስራ ሂደቶች አንዱ በመሆኑ የክልሉን የትምህርት ግብዓቶች የሚመለከቱ ሥራዎች ዘመናዊ ሥርዓትን ተከትለው እንዲከናወኑ በመምራት፣ አቅራቢዎችን እና ተጠቃሚዎችን በማስተሳሰር፣ የክልሉን የትምህርት ጥራት በውጤታማነት ለማሳደግ የሚሰራ ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

በመሆኑም ከትምህርት ተቋሞች የሚሰበሰበውን የግብአት ፍላጎት መሰረት አድርጎ ከተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ አገር እቅራቢዎች ጋር ግንኙነት ፈጥሮ የመንግስትን ጥቅም ሊያስጠብቅ በሚችል መልኩ ግዥ የሚፈጸምበት ወይም ከፍተኛ የሆነ የክልሉ ሀብት ሞብላይዝ የሚደረግበት እና ፍትሀዊነቱን በጠበቀ መልኩ የትምህርት ግብአት ድልድልና ስርጭት የሚደረግበት በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረትና ጥንቃቄ በማድርግ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

  1. የዳይሬክቶሬቱ ተልኮ፣ አላማ፣ ተግባርና ሀላፊነት፣ ተደራሽ ግብ
  • ተልኮ፡-የአብክመትምህርት ቢሮ ዋና ደንበኛ/ተማሪው በተደራጀ እና በተሟላ የትመህርት ግብአት እንዲማር ማስቻል ነው
  • አላማ፡- የዳይሬክቶሬቱ ዋና አላማ በክልሉ ያሉ የትምርት ተቋማት የብቁ ዜጋ ማፍራት ተልኳቸውን መሳካት የሚያስችል ፈጣን ጥራትና ወጭ ቆጣቢ የሆነ ደንበኛውን ሚያረካ የትም/ግብአቶችን በማቅረብ የተማሪዎችን የትምህርርት አቀባበልና ፈጠራ ስራ እንዲሻሻል ማድረግ ነው፡፡
  • የዳይሬክቶሬቱ ዋና ግብ (Streetch Objective) በሁሉም ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎች ደረጃውን የጠበቀ የትመህረት ግብአት በመሟላቱ የተማሪዎች ውጤት ተሸሽሏል፡፡
  • የዳይሬክቶሬቱ ተግባርና ሀላፊነት

የትምርት ግብአቶች በግዥ በእርዳታ እና በጥገና የሚቀርቡ ሲሆን የዳይሬክቶሬቱ ዋና ዋና ተግባርና ሃላፊነቶች ምን ምን እንደሆኑ ከዚህ በታች ተዘርዝሮ ቀርቧል፡፡

  • የፍላጎት መረጃ ከሚመለከታቸው አካላት ያሰባስባል
  • ፍላጎቱን መሰርት አድርጎ በጀት መያዙን ያረጋግጣል፡፡
  • የግዥ እቅድ ያዘጋጃል/ያጸድቃል
  • የግዥ ህጉን መሰረት አድርጎ የግዥ ዘዴ ይለያል፣
  • የግዥውን ሂደት ከሰነድ ዝግጅት እስከርክክብና ስርጭት ያለውን ሂደት በመከታተል ይፈጽማል ያስፈጽማል
    1. የዳይሬክቶሬቱ አደረጃጀት
      • በእርዳታ፣ በግዥ እና በተለያዩ መንገዶች የሚገኙ የትም/ግብአቶች በተፈለገው ጊዜ እና ቦታ አገልግሎት እንዲሰጡ ያጓጉዛል አስፈላጊውን ክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል(ለክዘና ማእከላት፣ ለዞን ትም/መምሪያ፣ ለወረዳ እና ለትም/ቤቶች)
      • የግብአት መረጃዎችን(ያለፉትን፣ ያሁኑን እና የወደፊቱን)ያደራጃል ይተነትናል ለሚመለከተው አካል እንደአስፈላጊነቱ ያቀርባል፡፡
      • አዲስ የትም/መሳ/ክዘናና ስርጭት ማእከላትን ሲቋቋሙ ማደራጀትና ወደስራ የማስገባት
    • በክልል፡- ተግባሩ በክልል በዳሬክቶሬት ደረጃ የሚመራ ሲሆን ያሉት የስራ ክፍሎች
    • የግብአት ጥናትና አቅርቦት ኬዝ ቲም
    • ድልድል ስርጭትና ክትትል ኬዝ ቲም
    • ንብረት ምዝገባና ቁጥጥር ኬዝ ቲም
      • በማእከል ደረጃ 5 የክዘናና ስርጭት ማእከል ሲኖሩ እነሱም
        • የደብረማርቆስ ክዘናና ስርጭት ማእከል፡- አገልግሎት የሚሰጠው
      • ለምስራቅ ጎጃም፣
      • ለምእራብ ጎጃም፣
      • ለአዊ እና ለባህርዳር ከተማ አስተዳደር ነው
        • ጎንደር ክዘናና ስርጭት ማእከል፡- አገልግሎት የሚሰጠው
      • ለሰሜን ጎንደር፣
      • ለማእከላዊ ጎንደር፣
      • ለምእራብ ጎንደር እና ለጎንደር ከተማ አስተዳደር
        • ደሴ ክዘናና ስርጭት ማእከል፤- አገልግሎት የሚሰጠው
      • ለደቡብ ወሎ
      • ለኦሮምያ እና ለደሴ ከተማ አስተዳደር
        • ወልድያ ክዘናና ስርጭት ማእከልአገል፡- ግሎት የሚሰጠው
      • ለሰሜን ወሎ፣
      • ለዋግ ኸምራ
        • ደብረብርሀን ክዘናና ስርጭት ማእከል፡- አገልግሎት የሚሰጠው
      • ለደብረብርሀን