Human Resource management

የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

የሰው ሀብት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቀደም ሲል ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ያለና በተለያየ ስያሜና መጠሪያ ለተቋሙ ራዕይና ተልዕኮ መሳካት በኩል የራሱን ድርሻ በመወጣት ያለው አስተዋጽዖ ከፍተኛ ሲሆን ስያሜውም ዘመኑ ከደረሰበት ዕድገት ጋር እንዲሄድ በማድረግ አሁን ላይ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመባል ይጠራል፡፡

ዓላማ፤

ይህ ሂደት ለተቋሙ ራዕይና ተልዕኮ መሳካት አኳያ ከሠራተኞች/ሥራ ፈላጊዎችን/ በመጋበዝ የሰው ኃይል ስምሪት በችሎታ፤በብቃት በግልጽነትና ከአድልዎ ነጻ የሆነ ውድድር በማካሄድ በብቃት ላይ የተመሰረተ እንዲሆንና የማማከር ሥራ፤

አመልካቾች በችሎታቸው ለመወዳደር እኩል ዕድል የሚያገኙበትን የአሰራር በመዘርጋት ተግባራዊ እንዲሆን፤

በተቋሙ የሚገኙ ሠራተኞችን ወርሃዊ ደመወዝን ጨምሮ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን እንዲያገኙ የማድረግ፤

መብታቸው እንዲከበርላቸው የተሟላ መረጃ በመያዝ የበኩሉን አስተዋጽዖ በማድረግ በኩል ጉልህ ድርሻ ያለው፤

የሠራተኞችን ውስጣዊ ብቃት ለማሳደግ የረጅምና የአጭር ጊዜ የሥልጠና ዕድሎች ሲኖሩ ከአድልዎ ነጻ የሆነ ውድድር ማካሄድ፤

አዳዲስም ሆነ ነባር መዋቅር ሲፈጠር  በሰው ኃይል እንዲሟላ የሥራ መደቦችን የሥራ ዝርዝር ማዘጋጀትና  የሥራ መደቡን ማስፈቀድ፤

አዳዲስ የትምህርት ዝግጅቶችና የሥራ ልምዶች ሲቀርቡ ተገቢነታቸውን በማየት ከበቂ ማብራሪያ ጋር አስተያየቶችን ለኮሚሽኑ በማቅረብ እንዲካተቱ ማድረግ፤

በተቋሙ ሠራተኞች መካከል በሥራ ላይ የአሰራር ግድፈት ሲከሰት ህግን መሰረት በማድረግ አጣርቶና መርምሮ  አስፈላጊው የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ የማድረግ፤