Curriculum preparation & Implementation

ዳራ

ትምህርት ቢሮዉ በአዋጅ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት የተለያዩ ስያሜዎች ተሰጥተውት የመማሪያ ማስተማሪያ መጻሕፍት ዝግጅትንና ሌሎችንም ተግባራት ሲያከናውን ቆይቷል። በዚህም ከ1985-ጥር1989 ዓ.ም የስርዓተ ትምህርት ጥናትና ዝግጂት መምሪያ፣ ከየካትት1989-1994 ዓ.ም ድረስ የስርዓተ ትምህርት ዝግጂት ጥናትና ምርምር መምሪያ፣ ከመስከረም 2000 ዓ.ም-ጥቅምት 2001 ዓ.ም የስርዓተ ትምህርት ዝግጂት የትምህርት ምዘናና ጥናትና ምርምር መምሪያ፣ ከዚያም በመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ (BPR) ጥናት መሠረት ከህዳር 2001 ዓ.ም ጀምሮ የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዋና የሥራ ሂደት በሚል ስያሜ ተዋቅሮ ሲጠራ ቆይቷል። ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በተካሄደዉ የነጥብ የስራ ምዘና (JEG) ጥናት ደግሞ የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት በሚል ስያሜ በአዲስ መልክ እንዲደራጅ ተደርጓል።

አደረጃጀት

የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት በትምህርት ቢሮ ከተቋቋሙት 15 ዳይሬክቶሬቶች መካከል አንዱ ነው። ዳይሬክቶሬቱ በአንድ ዳይሬክተር የሚመራ ሲሆን በስሩ አራት ቡድኖችን ማለትም የቋንቋና የማህበራዊ ሳይንስ ቡድን፣ የሂሳብና የተፈጥሮ ሳይንስ ቡድን፣ የፈተናና ምዘና ቡድን እና የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ቡድንን ይዟል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የትምህርት ቤት ማሻሻያ መርሀግብር እና ስርዓተ ምግብ የየራሳቸዉ አንዳንድ በባለሙያ ተመድቦ በስሩ ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ በእያንዳንዱ ቡድን የተመደቡትን ባለሙያዎች እና አንድ ጸሐፊን ጨምሮ  26 የሰዉ ሀይል  አሉት። በዚህ አደረጃጀት ዳይሬክቶሬቱ የተሰጠውን ተልዕኮ እየተወጣ ይገኛል፡፡

 ግቦች

  • በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች 50% እና ከዚያ በላይ፣ 30% የሚሆኑት 75% እና በላይ፣ 15% የሚሆኑት 85% እና በላይ ውጤት ማስመዝገብ የቻሉ ተማሪዎችን ማፍራት፣
  • ውጤታማ ሥራን ሊሠራና ሥራ ፈጣሪም መሆን የቻለ፤ በደረጃው በሀገር ዓቀፍና በዓለም አቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ የሆነ፤ በመልካም የዜግነትና የሥነ-ምግባር ዕሴቶች የታነፀና ለክልሉ ብሎም ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ሁለንተናዊ ልማትና ፈጣን ዕድገት ጉልህ አስተዋፅዖ ሊያደርግ የሚችል ዜጋ ማፍራት፣

ዓላማዎች

  • የኅብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ፍላጎቶች መሠረት ያደረገ አገር አቀፋዊ እና ዓለም አቀፋዊ ደረጃውን የጠበቀ ሥርዓተ ትምህርት በመቅረፅ የመማር ማስተማሩን ክንውን ስኬታማ ማድረግ፣
  • መልካም አስተዳደራዊና ዲሞክራሲ በሰፈነበትና ተማሪን ማዕከል ባደረገ የትምህርት አሰጣጥ ውጤታማነትን ማጎልበት፣

ዋና ዋና ተግባራት፡-

  • የዳይሬክቶሬቱን ማስፈፀሚያ ዕቅድ ማዘጋጀት፣
  • ከቅድመ መደበኛ እስከ መካከለኛ ደረጃ ለሚሰጡ የትምህርት አይነቶች የመፃህፍት ዝግጅት እንዲካሄድ ማድረግ፣
  • የመፃህፍት ህትመትና ስርጭትን መከታተል፣
  • ስርዓተ ትምህርቱን ከመረጃ ቴክኖሎጅ በተጨማሪ በንባብና የማጣቀሻ መፃህፍት፣ በቤተ ሙከራ ማንዋሎች መደገፍ፣
  • የክፍል ውስጥ የመማር ማስተማር ክንውንን መከታተልና መደገፍ፣
  • የክፍል እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ክልላዊ ፈተናን ማዘጋጀት ማስተዳደር እና ውጤት መግለፅ፣
  • አገር አቀፍ ፈተና ሲካሄድ የሚያስፈልገውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣
  • በሥርዓተ ትምህርቱ አተገባበር ዙሪያ ጥናትና ምርምሮች እንዲካሄድ ማደፍረግ፤ የጥናት ውጤቶችን መሰረት ያደረጉ ምክረ ሀሳቦችን ለሚመለከተዉ አካል እንዲቀርቡ ማድረግ፣
  • የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ጥራቱን ጠብቆ በፍትሐዊነት በሁሉም ዞንና ወረዳ እንዲስፋፋና ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችሉ የተለያዩ ስልቶችን በመቀየስ መተግበር፣
  • የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት ተሳትፎን በሚያሳድጉና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን በሚያጎለብቱ ተግባራት ላይ መስራት፣
  • የትምህርት ቤት መሻሻል መርሃ ግብር በትምህርት ቤቶች በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን፣

ለአገልግሎት ፈላጊዎች ስልክ ቁጥር፡-

  • የዳይሬክተር ቢሮ———————————– 0582204747/ 0582206525
  • ቋንቋና ማህበራዊ ሳይንስ ቡድን———————- 0583206897
  • ሂሳብና ተፈጥሮ ሳይንስ ቡድን
  • ፈተናና ምዘና ቡድን——————————– 0582262370
  • የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ቡድን—————— 0582207886