General Education Inspection Monitoring & Evaluation

1.  ዳራ

መንግስት ሰፊ መሰረት ያለው ፈጣን፣ ቀጣይነትና ፍትሃዊነቱ የተረጋገጠ የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ልማትን የማፋጠንና ድህነትን የማስወገድ ዓላማ ያለው ሲሆን ባለፉት  ዓመታት የአገሪቱን አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለመምራት የሚያስችል  የረጅምና የመካከለኛ ዘመን የልማት እቅድ ተዘጋጅቶ በመተግበር ላይ ነው፡፡

በሀገር ደረጃ የተነደፉ የልማት እቅዶችን ለመተግበር በሁሉም ደረጃ የሚያስፈልገውን የማስፈፀም አቅም ማሳደግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ትምህርትን በየደረጃው ማስፋፋትና ጥራቱን ማረጋገጥ የግድ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በትምህርቱ ዘርፍ የቅድሚያ ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች አንዱ አጠቃላይ ትምህርት ነው፡፡ ስለሆነም በ1986 ዓ.ም  የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ በመቅረፅ እና ፖሊሲውን ስራ ላይ ለማዋል ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ በተነደፉ/በተዘጋጁት ተከታታይ የትምህርት ዘርፍ ልማት ፕሮግራሞች የትምህርት ተደራሽነትን፣ ፍትሀዊነትን እና አግባብነትን በየደረጃው ከማሳደግ አኳያ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡

ትምህርትን ከማስፋፋት ጎን ለጎን ጥራቱን ለማረጋገጥ የሚረዱ ስልቶችን በመንደፍ በትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማሩ አጋዥ የሆኑትን የትምህርት ግብዓት፣ ሂደትና ውጤት በማሻሻል የተማሪዎችን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ለማጎልበት  በ1999 ዓ.ም የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ ተቀርፆ በሁሉም የሀገራችን ክልሎች በመተግበር ላይ ነው፡፡ ፓኬጁ  የመምህራን ልማት፤ የሥርዓተ ትምህርት፣ መጻህፍትና ምዘና፤ የትምህርት ቤት መሻሻል፣ የትምህርት አመራርና አስተዳደር፤ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ እንዲሁም የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር መርሀ ግብሮችን አካቷል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች  የመርሀ ግብሮቹን አፈጻጸም  ለመገምገም የሚያስችል የኢንስፔክሽን ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኗል፡፡

አለም አቀፍ ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት በትምህርት ቤቶች የሚካሄድ ተከታታይ ኢንስፔክሽን  የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻልና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ የኢንስፔክሽን የግምገማ ውጤት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ በተለይም ደግሞ የትምህርት ቤት ማሻሻያ መርሀ ግብር አተገባበርን በተመለከተ መረጃ የሚሰጥ ነው፡፡

ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በመንግስት የተሰጠውን ሃላፊነት መሰረት በማድረግ በ2005 ዓ.ም የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬትን ያቋቋመ ሲሆን የዚህ የስራ ክፍል ሃላፊነት ከክልል እስከ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች ጋር በመተባበር በክልሉ በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ በየደረጃው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የኢንስፔክሽን ስራ ለማከናወን የሚረዳ ሥርዓት መዘርጋት፣ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት እንደ አስፈላጊነቱ ሙሉ፣ ከፊል፣ ተከታታይና የተወሰነ ጉዳይ ላይ ያተኮረ የኢንስፔክሽን ስራ ያከናውናል፡፡

በዚሁ መሠረት ት/ቤቶች ያሉበትን የአፈጻጸም ደረጃ ከግብዓት፣ ሂደትና ውጤት አኳያ ለመመዘን የሚያስችል ሀገር አቀፍ የኢንስፔክሽን ማዕቀፍ በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን ማዕቀፉም በትምህርት ቤቶች ኢንስፔክሽን በምን መልክ መካሄድ እንዳለበት አጠቃላይ ሁኔታዎችን ሲያመለክት፤ይህ ሀገር አቀፍ የትምህርት ቤቶች ኢንስፔክሽን መመሪያ የማዕቀፉ ማሟያ ከመሆኑ በተጨማሪ በውስጡ የኢንስፔክሽን ሂደት፣ የአፈጻጸም ስልቶች፣ ከፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር እስከ ት/ቤት ድረስ ያሉ አካላት ሃላፊነትና የሥራ ድርሻ እንዲሁም የኢንስፔክተሮች ሙያዊ ስነምግባርን በውስጡ አካቶ ይዟል፡፡

2.  አጠቃላይ ዓላማ

የኢንስፔክሽን ዋና ዓላማ የትምህርት ጥራትንና ውጤታማነቱን በማረጋገጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተማሪዎችን ውጤትና ሥነምግባር ለማሻሻል ነው፡፡

3.  ግብ

በክልልላችን የሚገኙ ሁሉም የአጠቃላይ ትምህር ተቋማት ስታንዳርዳቸውን አሟልታ ማየት፡፡

4.  ተግባርና ኃለፊነት

  • በሀገር አቀፉ የኢንስፔክሽን ማዕቀፍና መመሪያ መሠረት የኢንስፔክሽን ተግባር ያከናውናል፡፡
  • ክልላዊ የኢንስፔክሽን ማዕቀፍ፣ ስታንዳርድ እና መመሪያዎችን የማዘጋጀትና የማሻሻል ሥራዎችን ያከናውናል፡፡
  • የትምህርት ቤቶች ኢንስፔክሽን ተግባር በአመታዊ የዕቅድ መርሃግብር መሠረት መከናወኑን ያረጋግጣል፡፡
  • የኢንስፔክሽን ሥራዎችን የተመለከተ የየሩብ ዓመት ሪፖርት ለትምህርት ሚኒስቴር ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት በወቅቱ ይልካል፡፡
  • በክልሉ/ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ የዞን/ ክፍለ ከተማ ትምህርት መምሪያና የወረዳ ት/ቤቶች ፅ/ቤት የኢንስፔክሽን ባለሙያዎች ስልጠና ያዘጋጃል፣ ይሰጣል፣ ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
  • በዞን ትምህርት መምሪያና በወረዳ ት/ቤቶች ፅ/ቤት ደረጃ የሚከናወኑ የኢንስፔክሽን ተግባራት በሀገር አቀፉ የኢንስፔክሽን ማዕቀፍና መመሪያ መሠረት ተግባራዊ መደረጋቸውን ይከታተላል፤
  • ከዞን ትምህርት መምሪያና ከወረዳ ት/ቤቶች ፅ/ቤት በየወሩ እየተዘጋጁ የሚቀርቡ የኢንስፔክሽን ሪፖርቶች ተገቢነትና የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ ስለመሆናቸው ያረጋግጣል፤
  • ከሁሉም ዞን ኢንስፔክሽን ዘርፍ የሚላኩ ሪፖርቶችን በማጠናቀርና በመተንተን የኢንስፔክሽን ተግባር ያስገኘውን ጥቅም ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፡፡
  • መልካም ተሞክሮዎች በመቀመርና በመለየት እንዲስፋፋ ያደርጋል፡፡
  • የኢንስፔክሽን መረጃ ይሰብስባል፣ ያደራጃል፣ ይተነትናል፣ ጥቅም ላይ ያውላል፤ ወቅታዊነቱን ይጠብቃል፡፡
  • በትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ተግባር ዙሪያ ጥናትና ምርምር ያከናውናል፡፡

5.  መዋቅራዊ አደረጃጀት