Audit

የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት አላማ

  1. የውስጥ ኦዲት ዓላማ የመስሪያ ቤቱ አመራርና ሰራተኞች ኃላፊነታቸውን በብቃት መወጣት እንዲችሉ በተዘረጋው የውስጥ ቁጥጥር ስርአትና በስራ ላይ ባሉ ትህጎችና የአሰራር ስርአቶች መሰረት ስራዎች መከናወናቸውን ኦዲት አድርጎ ማረጋገጥ ነው፡፡
  2. የውስጥ ኦዲት የተዋቀረው ዘመናዊ የኦዲት አተገባበር ሂደትን በመከተል የመስሪያ ቤቱን አሰራርና የውስጥ ቁጥጥር ስርአት በመገምገምና ስጋትን/ተጋላጭነትን/ በመፈተሽ ለመስሪያ ቤቱ ተጨማሪ እሴት /ፋይዳ/ የሚፈጥር ውጤታማ የሆነ ስራ ሊከናወን የሚችልበትን ዘዴ ለስራ አመራሩ የምክር አገልግሎት በመስጠት ለመስሪያቤቱ ዓላማ መሳካት አስተዋጽኦ ማድረግ ነው፡፡

የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት

  1. ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ተግባራትን ከመስሪያ ቤቱ ዓላማ ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ስጋት ተጋላጭነት ያለባቸውን የመስሪያ ቤቱን የስራ ክፍሎች መሰረት ያደረገ ዕቅድ ከሰው ኃይል አመዳደብ እና ከወጪ በጀት ፍላጎት ጋር አጠቃሎ በማዘጋጀት ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ አቅርቦ ማጸደቅና የኦዲት የስራ ትእዛዝ እና ሃሳብ በመስጠት እቅድና ፕሮግራም የማዘጋጀት፤
  2. የጸደቀው እቅድ በዚህ መመሪያ አንቀጽ ፭ ንኡስ አንቀጽ 2 በተመለከተው መሰረት አዘጋጅቶ ለሚመለከተው የማቅረብ
  3. የውስጥ ኦዲትን መደበኛ የኦዲት እቅድ ሁሉም ኦዲት ተደራጊ የስራ ክፍሎች እንዲያውቁት የማድረግ፤
  4. ኦዲተሮች ተለይቶ የሚሰጣቸውን የኦዲት ስራ በብቃት ለማከናወን የሚያስችላቸውን እውቀት፤ልምድ፤ ክህሎትና ሌሎች ተፈላጊ ችሎታዎች እንዲኖራቸው ማድረግና የስልጠና ፍላጎቶችን በማቀድና በበላይ ኃላፊ በማጸደቅ አፈጻጸሙን የመከታተል፤
  5. የተዘረጋውንየውስጥቁጥጥርሥርአትየመስሪያቤቱንዓላማዎችበከፍተኛቁጠባናውጤታማበሆነመንገድከግብለማድረስማስቻሉንበቂመረጃዎችንሰብስቦበመገምገምናበቁጥጥርስርአቱላይያለውንስጋትወይምተጋላጭነትበመለየትለመስሪያቤቱየበላይኃላፊየማሳወቅ፤
  6. በጸደቀው እቅድ መሰረት የኦዲት መጀመሪያ ስብሰባ እና ኦዲቱን አከናውኖ የኦዲት ማጠናቀቂያ ስብሰባ ከሚመለከታቸው ሰራተኞች ፤ የስራኃላፊወች እና የመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ጋር የማድረግ፤/እንደአስፈላጊነቱ/የመግቢያ ስብሰባው በእቅድ ባልተያዙ ኦዲቶች ላይ ላያስፈልግ ይችላል፡፡
  7. የተደረሰበትን ውጤት ድምዳሜና የማሻሻ ያሃሳቦች በሪፖርት ተገቢ ባህሪያት ላይ የተመሰረተ የተሟላ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ የማቅረብ፤
  8. አስቀድሞ በእቅድ ያልተያዘ ልዩ ኦዲት እንዲያደርግ በመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ሲታዘዝ ኦዲት ማከናወን፤
  9. በበጀት አመቱ መጨረሻ በመስሪያ ቤቱ አማካኝነት የተደረገውን ቆጠራ በፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ፤ ደንብና በመመሪያ መሰረት መከናወኑን በማረጋገጥ የቆጠራ ሪፖርቱን ከቆጠራ ሰነድ ጋር ለቢሮው እንዲቀርብ የማድረግ ይህንንም ለማድረግ በቆጠራ ወቅት በታዛቢነት በመገኘት በፈሰስ ሂሳብ ላይ የመሳተፍ፤
  10. ቀድሞ በቀረቡት የኦዲት ሪፖርቶች መሰረት የእርምት እርምጃ ያልተወሰደባቸውን ግኝቶች በመከታተል የእርምት እርምጃ እንዲወስዱ ክትትል የማድረግ፤
  11. የውጪ ኦዲተሮች በሚያቀርቧቸው ግኝቶች ላይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰዱ ክትትል ማድረግ፤
  12. በውስጥ ኦዲት የተከናወኑ ተግባራትን የሚገልጽ ወቅታዊ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት የማቅረብ ኃላፊነት፤

የትምህርት ቢሮ የኦዲት ዳይሬክቶሬት ስልክ ቁጥር 0582208450