የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ተዘዋውረን በተመለክተናቸው ትምህርት ቤቶቸ ፈተናው በሰላምና በተረጋጋ ሁኔታ እየተካሄደ ነው፡፡
ቢትወደድ አያሌው መኮንን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ሙሉቀን አንዷለም ተማረዎችን ቀድመው በስነ ልቦና እንዲዘጋጁ በማድረጋቸው ፈተናውን ተረረጋግተው መስራት እንዳስቻላቸው ነግረውናል፡፡
 
በዱርቤቴ ከተማ የሚገኘው ቢትወደድ አያሌው መኮንን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት 207 ተማሪዎችን እያስፈተነ መሆኑን የገለጹት ርዕሰ መምህሩ የአእምሮ ዉስንነት ላለባቸውና ማየት ለተሳናቸው ተማሪዎች አጋዥ ፈታኝ መመደቡን ገልጸዋል፡፡
ቢትወደድ አያሌው መኮንን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የፈተና አስተባባሪ የሆኑት አቶ የኔአለም መንግስቱ ፈተናው የፈተና ህግና ስርዓትን ባከበረ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
 
በሌላ በኩል የመራዊ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ወመህ አስተባባሪ አቶ ይታየው የልጆቻችንን ፈተና ለመታዘብና ተማሪዎች በስነ ልቦና ተረጋግተው እንዲፈተኑ ለማድረግ በትምህርት ቤቱ መገኘታቸን ነግረውናል፡፡
 
የመራዊ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ገበያው ልመንህ ያለፉ ትምህርቶችን መምህራን ለተማሪዎች በመከለስና ቤተ- መጽሃፍቱን ሁል ጊዜም ክፍት በማድረግ ተማሪዎች አንብበው እንዲዘጋጁ ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡
በመራዊ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት 393 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልላዊ ፈተናናውን እየወሰዱ ነው፡፡
 
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *