አቶ መቅደስ አክሊሉ የተባሉ ባለሃብት ከግማሽ ሚሊዬን ብር በሚበልጥ ወጭ በምስራቅ ጎጃም ዞን ለሚገኙ የሚሊሻ ቤተሰቦች ተማሪዎች 12ሽ ደብተር ድጋፍ አደረጉ፡፡
=========================================
አቶ መቅደስ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪና የዘሃብ ሆቴል ባለቤት ሲሆኑ በምስራቅ ጎጃም ዞን ለሚገኙ የሚሊሻ ቤተሰቦች ተማሪዎች 12ሽ ደብተር ድጋፍ ማደረጋቸውን የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ስለሽ ተመስጌን ገልጸዋል፡፡
እንደ መምሪያ ኃላፊው ገለጻ በዞኑ ውስጥ 3ሽ የሚሊሻ ቤተሰብ ተማሪዎች መኖራቸውን ገልጸው ባለሃብቱ፣ በጎ ፈቃደኞች አቅም ለሌላቸው ተማሪዎችና ለሚሊሻ ቤተሰብ ተማሪዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Via Infoeastgojjam
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau