ከጥቅምት29 እስከ ህዳር 2/2014 ዓ.ም ድረስ ሲሰጥ የቆዬው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሰላም ተጠናቅቋል፡፡
የ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በክልላችን ከወራሪው የህወሃት ቡድን ነጻ በሆኑ አካባቢዎች 124, 920 ተማሪዎች ፈተውን ወስደዋል፡፡
የ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ክልላችን አሁን ካለበት ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር በሰላም እንዲጠናቀቅ ከክልል እስከ ትምህርት ቤት ድረስ በቅንጅትና በትብብር ስትሰሩ ለነበራችሁ የፀጥታ አካላት፣ የፍትህ ተቋማት ፈተናው በሰላም እንዲሰጥ በዘርፉ ላደረጋችሁት ክትትል፣ የትምህርት አመራሮች፣ ፈታኝ መምህራን፣ የፈተና ተቆጣጣሪዎችና ወላጆች በሙሉ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ላደረጋችሁት አስተዋጽኦ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
ከምንም በላይ ፈተናው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ፈተናውን በትዕግስትና ዲስፕሊን የወሰዳችሁ ተማሪዎች የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለእናንተ ትልቅ ክብርና ምስጋና ያቀርባል፡፡
በአንዳንድ አካባቢዎች ተማሪዎች ዩኒፎርማቸውን ረዳት ለሌላቸው ተማሪዎች አሰባስበው ሰጥተዋል፡፡
ወራሪው የትግራይ ሃይል በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች የምትገኙ ተፈታኝ ተማሪዎቻችን በቅርብ ጊዜ ተለዋጭ ፈተና ተዘጋጅቶ የሚሰጣችሁ በመሆኑ በስነ ልቦና ጠንክራችሁ በቀጣይ ለሚሰጠው ተለዋጭ ፈተና እየተዘጋጃችሁ እንድትጠብቁ እናሳስባለን፡፡
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse