“ቤተሰባዊ መማማር፣ ሀገር-በቀል አስተምህሮ እና በማህበረሰብ መማማሪያ መዕከላት አመሰራረት” ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተካሄደ፡፡
*************************************************************************
በስልጠናው ከሁሉም የኢትዮጱያ ክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች፣ከ12ቱ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ባለሙያዎች፣ ከትምህርት ሚኒሰቴር የዘርፉ ባለሙያዎችና ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዉበታል፡፡
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና ስነ ባህሪ ኮሌጂ ዲን ተወካይ አቶ ቆየ ካሳ ለስልጠናዉ ተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ አቶ ቆየ ስልጠናዉ ለማህበረሰቡ ከቀለም ትምህርት ባለፈ የህይወት ክህሎት ትምህርት መሰጠት አለበት ብለዋል፡፡
በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የጎልማሶች ትምህርትና ማህበረሰብ ልማት መምህርና የምርምር ቡድኑ አባል አቶ ኤርሚያስ ፀሐይ ስለ ቤተሰባዊ መረዳትና ተስተምህሮ ምንነት ፣ ይዘት፣ ዋና ዋና አላማዎችና ጠቀሜታዉ ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ተሳታፊዎችም በርዕሰ ጉዳዩ ላይ በጋራ በመወያየት የየራሳቸዉን ተሞክሮ በማንሳት በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ በበኩላቸዉ በአሁኑ ሰዓት ትምህርት ሚኒስቴር ዘርፉን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀዉ የሁሉም ክልል የስራዉ ባለቤቶች በስልጠናዉ በመታገዝ ከወትሮዉ በተለየ መልኩ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ በሚኒሰቴር መ/ቤቱ ስም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የዩኒስኮ ቼር ኢትዮጱያ አስተባባሪና የጥናት ቡድኑ መሪ ረ/ፕሮፌሰር ጥሩወርቅ ዘላለም በዉይይቱ ላይ በመገኘት “ በአፍሪካ የጎልማሶች ትምህርት እናት ” በመባል የሚታወቁትን የፕሮፌሰር ላላግ ባዉን የህይወት ተሞክሮ በማንሳት ፕሮፌሰሯ ላበረከቱት በጎ አስተዋፅኦ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የፕሮፌሰር ላላግ ባዉን ስራዎችና የህይወት ተሞክሮም ለተሳታፊዎች ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል፡፡
በዉይይቱ ማጠቃለያ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደ ዩኒቨርሲቲዉ የጎልማሶችን ትምህርት ለማጠናከር ከቅድመ ምረቃ እስከ ድህረ ምረቃ እያስተማረ ይገኛል ብለዋል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተስፋዬ ሽፈራዉ በበኩላቸዉ የጎልማሶች ትምህርት ሁሉም ሰዉ ሊሳተፍበት እንደሚገባ ገልፀዉ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲም ዘርፉን ለማሳደግ ከዩኒስኮ ጋር በጋራ እየሰራ ነዉ ብለዋል፡፡በዚህም የባህር ዳር ከተማ የትምህርት ከተማ ተብላ በዩኒስኮ እንድትመዘገብ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡ ዶ/ር ተስፋዬ አክለዉም አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ሲዘጋጅ የጎልማሶች ትምህርት እንዲካተት ተደርጓል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የስልጠናዉ አስተባባሪ ረ/ፕሮፌሰር ዐብይ መንክር “ የጎልማሶች ትምህርትና የእድሜ ዘመን ትምህርት ማህበር ” በማቋቋም ዘርፉን ለመደገፍ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ጠቅሰዉ የሚመለከታቸዉ አካላት የማህበሩ አባል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ምንጭ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በቴሌግራም https://t.me/anrse