ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከአማራ ምሁራን መማክርት ጋር በመተባበር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የስርአተ ትምህርት ለውጥ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
አዲሱ ስርአተ ትምህርት ሙሉ በሙሉ በምሁራን ተሳትፎ የተዘጋጀ ከመሆኑም ባሻገር ሁሉም ባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጡበት ጥረት ተደርጓል፡፡
ይህ ስርዓተ ትምህርት ባለፉት ወራት በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የሙከራ ትግበራ ተካሂዶ ከመምህራን አስተያየቶች ተሰብስበዋል፡፡
ቢሮው የመፀሀፍቶች የመጨረሻቸውን ቅርጽና ይዘት ይዘው ከመውጣታቸውና ተግባራዊ ከመሆናቸው በፊት ከመላው ህዝብ አስተያየቶችን መቀበል ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም አዲሶቹ መፀሀፍቶች በቢሮው ድረ-ገጽ www.anrseb.gov.et የተጫኑ በመሆኑ ከዛሬ ጀምሮ መጸሀፍቶችን በመመልከት ማነኛውንም አስተያየት በውስጥ መስመር ወይም በአስተያየት መስጫ እንዲያደርሱን ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
በዚህ ታሪካዊ ስራ ስለተሳተፉና የዜግነት ሀላፊነትዎትን ስልተወጡ በአማራ ክልል ተማሪዎች ስም ምስጋናችን የላቀ ነው፡፡
አስተያየት ሲሰጡ በትምህርት አይነትና በክፍል ደረጃ ለይተው እንዲሰጡ ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡
የቀጣዩ ትውልድ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በእኛው እጅ ነው!!
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
ሸር ሸር ሸር………..
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *