በሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከ90 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ በጀት የማስፋፊያ ግንባታ ሊካሄድ ነው፡፡
በዋግሕምራ ብሔረሰብ ዞን በሰቆጣ ከተማ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች የማስፋፊያ ግንባታ እንደሚካሄድ ከዞኑ ትምህርት መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከትምህርት ሚኒስቴርና ከአጋር አካላት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የማስፋፊያ ግንባታቸው የሚካሄድባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል በቅርቡ ስሙን የቀየረው የሰቆጣ አጠ/2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት በአሁኑ ስያሜው ኮሎኔል አማረ ሞላ አጠ/2ኛ ደረጃና የከ/ትም/ት መሠናዶ ት/ቤት የማስፋፊያ ግንባታው በጀት 50 ሚሊዮን ብር ሲሆን ወጭውም በትምህርት ሚኒስቴር የሚሸፈን ይሆናል፡፡
በማስፋፊያ ግንባታው የጤና እና የግብርና ፓኬጆችን ያካተተ ነው፡፡ የማስፋፊያ ግንባታው የመማር ማስተማሩን ሂደት ውጤታማ ከማድረግ በተጨማሪ የአካባቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ይጠበቃል።
በመድሃኒዓለም አጠ/1ኛ ደረጃ ት/ቤት በ9.9 ሚሊዮን ብር የሚገነባው የማስፋፊያ ግንባታ የቤተ ሙከራ፣ ቤተ መጽሃፍትና እና ሌሎችንም ክፍሎች የሚያካትት ሲሆን በፌዴራል የከተሞች የምግብ ሴፍቲኔት ፕሮግራም እንደሚገነባም ታውቋል፡፡
በሌላ በኩል በዋግ ስዩም አድማሱ ወሰን አጠ/2ኛ ደረጃና መሠናዶ ት/ቤት በድሮ አጠራር በሰላም ሚኒስቴር ባለ አንድ ፎቅ የመማሪያ ክፍል ይገነባል፡፡
ግሪን ኢንሸቲቨ ኢትዮጵያ በተባለ ግብረሰናይ ድርጅት የመማሪያ ክፍሎች የማስፋፊያ ግንባታ የሚካሄድበት የአባ ዮሃንስ የመ/ደ/ት/ቤት መሆኑ ከዞኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ በጽባያና በመድሃኒዓለም የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች በአመልድና በሰቆጣ ቃል ኪዳን ስምምነት ድርጅት የመፀዳጃ ቤት ግንባታዎች ይካሄዳሉ፡፡
ከሰሞኑ በከተማ አስተዳደሩ ማይቡሊት በሚባል አካባቢ አዲስ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በGlobal Alliance Ethiopia በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ አልማ እና ዋልማ በጋር በመተባበር ለሚያስገነቡት ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋ ማስቀመጡ የሚታወስ ነው፡፡
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse