ስለ 12ኛ ክፍል ተጨማሪ መረጃ
።።።።።።።።።።።።።።።።
1. አማራ ክልልን በተመለከተ በጦርነት አካባቢ የነበሩ ማለት የክልሉን ሁሉንም ዞኖች ማለት ነው። መጀመሪያ ቅሬታ እና ክርክሩ የተነሳው ከአማራ ክልል ብቻ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም በክርክራችን መሰረት በልዩ ሁኔታ ውሳኔው ሁሉንም የክልሉን ተማሪዎች እንዲያካትት የተደረገው ለአማራ ክልል ብቻ ነው። ይህ ማለት ወደ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ያላመጡት ሁሉም የክልላችን ተማሪዎች በመደመበኛ ተማሪነት ፈተናውን በድጋሜ ይወስዳሉ ማለት ነው።
2. ተጨማሪ የተወሰነላቸው 4339 ተማሪዎች ደግሞ 50 ፐርሰንት እና ከዛ በላይ ካመጡ ከክልላችን ሁሉም ዞኖች መካከል ተማሪዎች በውጤታቸው ቅደም ተከተል የሚመረጡ ይሆናል።
3. ይህ በዚህ እንዳለ ሌሎች 50 ፐርሰንት እና በላይ ውጤት አምጥተው ወደ ዩኒቨርስቲዎች መግባት ያልቻሉት ደግሞ በክልላችን መምህራን ኮሌጆቾ በመደበኛው የዲግሪ ኘሮግራም የመምህርነት ስልጠና እንዲጀምሩ ሰፋ ያለ ቁጥር ለመቀበል ዝግጅት እያደረግን ነው።
4. በዚህ ሁሉ ጥረት ውስጥ ወደ ዩኒቨርስቲዎችም ሆነ ወደ መምህራን ኮሌጆቾ መግባት ያልቻሉት ተማሪዎቻችን በቂ ዝግጅት አድርገው መፈተን እንዲችሉ የ2014 ዓም የ12ኛ ክፍል የፈተና ጊዜ እንዲራዘምልን ለትምህርት ሚኒስቴር ባቀረብነው ጥያቄ መሠረት ከመስከረም 2015 ዓም በፊት ፈተናው እንደማይሰጥ በትናንትናው ዕለት ተወስኗል።
ስለሆነም የተከበራችሁ የክልላችን ተማሪዎች የ2014 ዓም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 20 ቀን 2015 ዓም ጀምሮ ባሉት ጊዚያት ሊሰጥ እንደሚችል አውቃችሁ ተገቢውን ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳሰብን በቢሮው በኩል አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ የሚደረግ መሆኑን እናረጋግጥላችኋለን።
ማተብ ታፈረ (ዶር)
ቢሮ ሀላፊ