ሚያዝያ 26/2014
።። ደሴ።።።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከትምህርት ባለ ድርሻ አካላት ጋር የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም፣ የመጀመሪያው ወሰነ ትምህርት ውጤት ትንተና፣ በ2014 የትምህርት ዘመን ተፈታኝ ተማሪዎች የንቅናቄ እቅድ ዙሪያ በደሴ ከተማ ውይይት እያካሄደ ነው። ውይይቱ እሰከ ሚያዝያ 27/2014 ድረስ የሚቀጥል ሲሆን በውይይቱ መጨረሻ በ2013 የትምህርት ዘመን ወደ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 600 እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ይበረከትላቸዋል።
የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅምዎ የፈቀደውን የብር መጠን ጽፈው ወደ 9222 ይላኩ።
በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥራችን 9222 ን ይጠቀሙ በተጨማሪም በቴሌብር ዓለምአቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም የድርሻዎን ይወጡ።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse