የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ከግል ትምህርትቤቶች ጋር ውይይት አካሄደ።
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ከግል ትምህርትቤቶች ጋር በአገልግሎት አሰጣጥና ክፍያ መመሪያ ላይ ውይይት አድርጓል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ የወጣውን የግል ትምህርት ተቋማት የትምህርት አገልግሎት አሰጣጥና የክፍያ አፈጻጸም መወሰኛ መመሪያ ቁጥር 06/2014 ዓ.ም ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።
የግል ትምህርት ተቋማት የትምህርት ቤት ክፍያ አፈጻጸም በመመሪያው መሰረት እንዲፈጸም መግባባት ላይ ተደርሷል።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መኳንንት አደመ የግል ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን በእውቀት፣ በስነ ምግባርና በክህሎት ለማብቃት ዓልመውና አቅደው መስራት እንደሚገባቸው ገልጸዋል።
የግል ትምህርት ቤቶች የወላጅ መምህር ህብረት አባላት በትምህርት ተቋማትና በወላጆች መካከል ድልድይ ሆኖ የሚያገለግል በመሆኑ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ በኃላፊነት ስሜት ሊሰሩ እንደሚገባ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን ገልጸዋል።
የባሕር ዳር ከተማን የሚመጥኑ ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ የመንግስትና የግል የትምሕርት ተቋማት እንዲኖሩ ለማስቻል ቅንጅታዊ አሰራሮችን መከተል እንደሚገባ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ሙሉዓለም አቤ ገልጸዋል።
ለሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ደረጃቸውን ያላሟሉ የግል ትምህርት ተቋማት መኖር እንደሌለባቸው መምሪያ ኃላፊው አሳስበዋል።
የግል ትምህርት ቤቶች ማህበር ተወካይ አቶ ቢልልኝ በቀለ የግል ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁሉ በትብብር እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ ።
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *