ትምህርት የነጻነትና የሉዓላዊነት መገለጫ ነው፡፡ ዶክተር ሙሉነሽ ደሴ
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከኪነ ጥበብ፣ ኮሙኒኬሽን፣ሚዲያና የህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በትምህርት ለትውልድ ላይ የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ሙሉነሽ ደሴ ትምህርት የነጻነትና የሉዓላዊነት መገለጫ መሆኑን ተናግረዋል።
አሁን ላይ የክልሉን የትምህርት ሥራ አደጋ ላይ የጣሉ ወቅታዊ እና ነባር ችግሮችን ማጋጠማቸውን የገለጹት ዶክተር ሙሉነሽ በተለይም ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ነባሩን የትምህርት ሥርዓት ችግሮች በፍጥነት ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት ውስብስብ እንዲሆን ማድረጉን ገልጸዋል።
በክልላችን እያጋጠመ ያለው መማር ማስተማርን የማወክ እንቅስቃሴ ከሕዝብ መራቅን የሚያመላክት መሆኑን የተናገሩት ኃላፊዋ በመምህራንና በትምህርት አመራሮች ላይ እየደረሰባቸው የሚገኘውን እንግልት፣ እገታና ግድያ ህብረተሰቡ ሊያወግዝ እንደሚገባ አስገንዘበዋል፡፡
የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መንገሻ ፈንታው በክልሉ ትምህርት ላይ እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት ከህብረተሰቡ ጋር የጋራ መግባባት መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ይህን የጋራ መግባባት ለመፍጠር የኪነ ጥበብ፣ ኮሙኒኬሽንና የሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች ኃላፊነታቸው በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *