በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የጭልጋ ወረዳ የሰራቆ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምቹ የመማሪያ ክፍልን ለመፍጠር ባለ 3 የመማሪያ ክፍል በህብረተሰብ ተሳትፎ በመገንባት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎችን ለመማር ማስተማር ዝግጁ መሆኑን የሰራቆ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገለፀ።
ለትምህርት ጥራት መምጣት ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎችን ትኩረት አድርጎ እየሰራ ያለው ትምህርት ቤቱ የተማሪዎች ቁጥር በመጨመሩ ምክኒያት አሁን ከአለው የመማሪያ ክፍል ተጨማሪ የክፍል ግንባታ በማስፈለጉ ምክኒያት ህብረተሰቡን በማስተባበርና በቅማንት ልማት ማህበር የበጀት ድጋፍ 420ሺ 818 ብር ወጭ በማድረግ ግንባታውን በማጠናቀቅ ለመማር ማስተማር ዝግጁ መሆኑን የትምሀርት ቤቱ ር/መ/ር ቄስ አይምሮ ተሾመ ገልፀዋል።
የትምህርት ተቋም ያለማህበረሰብ ተሳትፎ አቅም የሌለው መሆኑ በየትምህርት ቤቶች በህብረተሰብ እየተገነቡ ያሉ የመማሪያ ክፍል ግንባታዎች ህብረተሰቡ የትምህርት ቤት ባለቤት መሆናቸውንና የትምህርት አመራሩ ቅንጅታዊ አስራር መኖሩን የሚያመላክት መሆኑን በምርታት ስነስርዓት ጊዜ ተነስቷል።
የክፍል ግንባታው ምርቃት ላይ የአይከል ከተማ ከንቲባ አቶ ወርቁ ጎሼ ፣የጭልጋ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ንጉሴ እና ሌሎች የትምህርት ፅ/ቤት ማንጅመንት አካላትና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የምርቃት ስነስርዓቱ ተካሂዷል።
+3
See insights and ads

Boost post
<img class="x16dsc37" role="presentation" src="data:;base64, ” width=”18″ height=”18″ />
All reactions:

51

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *