*********************
በሰሜን ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ በርካታ የልማት ስራዎች ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን ተገለፀ።
በሞረትና ጅሩ ወረዳ የወይራ አምባ ኮፕሬሲቭ ጤና ኬላና ባለ ሁለት ወለል የጅሁር አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ ተጠናቆ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተሞች ክላስተር አስተባባሪ እና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አህመዲን መሐመድ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሀላፊ ኢብራሂም መሐመድ(ዶ/ር)፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ ፣ የዞንና የወረዳ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።
በ10.5 ሚሊየን ብር የተገነባው የጅሁር አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የትምህርት ተሳትፎንና ፍትሐዊነትን በወረዳው ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት እንደሚመልስ ተገልጿል። የግንባታ ወጭውም በወረዳው አልማ እና በአካባቢው ተወላጆች የገንዘብ ድጋፍ እንደሆነ ተገልጿል።.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *