“አልማ ለትምህርት ጥራት ትኩረት ሰጥቶ መማሪያ ክፍሎችን ሰለገነባልን እናመሰግናለን”
በለምለም ተራራ የሚገኙ የአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪወች
በምዕ/ጎ/ዞን መተማ ወረዳ በለምለም ተራራ ቀበሌ በአልማ እና በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነቡ መማሪያ ክፍሎች የዞንና ወረዳ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የሚመለከተው አካላት በተገኙበት ተመርቋል።
የምዕ/ጎ/ዞን ም/አስተዳዳሪ እና ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ አንዳርጌ ጌጡ በጋራ ተቀናጅተን በመስራታችንና የለምለም ተራራ ህዝብ ሰላሙን በራሱ አቅም ያረጋገጠ በመሆኑ ዛሬ ላይ የልማት ፍሬወችን ለመመረቅ በቅተናል ያሉ ሲሆን፤ አልማም የመንግስትን የልማት ጉድለቶችን እየለየ በራስ አቅም የመልማት ፍላጎትን እያሳካ ያለ ትልቅ ማህበር በመሆኑን አመስግነዋል። ተማሪወችን በምቹ የመማሪያ ክፍል እንዲማሩ ከማድረግ ባለፈ ግብዓቶችን በማሟላት በቂ ድጋፍ በማድረግ ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እና ውጤታማ ዜጎችን ለማፍራት መምህራንና ወላጆች ከመንግስት ጋር በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
የመማሪያ ክፍል ግንባታው 4,500,000 ብር በላይ ወጭ እንደተደረገበት ተገልጿል።
የመተማ ወረዳ ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዛት ሰረፀ በበኩላቸዉ በለምለም ተራራ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለተማሪዎች ምቹ የመማሪያ ክፍሎች በአማራ ልማት ማህበር እና በህዝቡ ድጋፍ መገንባቱ የቀበሌዉ ህዝብ ከመንግስት ጋር ተቀናጅቶና ለሰላም አበክሮ በመስራቱ ነዉ ብለዋል።
አቶ ግዛት አክለዉም የቀበሌዉ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ለአልማ የሚያደርገዉን ድጋፍ በማጠናከር በትምህርት ዘርፍ ለሚደረገዉ ሁለንተናዊ እድገት የበኩላችሁን እንድትወጡ ሲሉ አሳስበዋል።
የምዕ/ጎ/ዞን ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ደሳለኝ አያና
ገዥ ሃሳብ አመንጭ በመሆን እና ህዝቡን በማስተባበርና በመስራት አልማ የጎላ አስተዋጽኦ አበርክቷል። የተማሪወችን ውጤት ለማሻሻል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለትምህርት ዘርፉ ተገቢዉን ድጋፍ መስጠት አለበት ብለዋል።
አልማን ፣ ወላጆቻችንና መንግስት በተሻለ ት/ቤት እንድንማር እና አካባቢያችን ሰላም ሆኖ ትምህርታችንን እንድንከታተል ስለደገፋቹህን እናመስግናለን ያሉት ደግሞ የለምለም ተራራ ተማሪዎች ናቸው።
የተማሪ ወላጆች በበኩላቸው የትምህርት ቤት ግንባታ ጥያቄያችን ተመልሷል በቀጣይ በትምህርት ላይ ያሉ ችግሮችን በመለየት ለመፍታት አብረን እንሰራለን አልማም ላደረገልን ድጋፍ እናመሰግናለን ብለዋል።
የወረዳው አልማ ቅ/ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ ያለው አልማ የራስን ችግር በራስ ለመፍታት አልሞ የሚሰራ ተቋም ነው ስለሆነም በቀጣይ ሁሉም የወረዳዉ ህዝብ የልማት ማህበሩ አባል በመሆን የመልማት ፍላጎታችንን ማረጋገጥ እንድንችል በትኩረት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
ግንቦት 17/2017
West Gondar zone Communication Affair Office

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *