በምስራቅ አማራ ዞኖች በሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የትምህርት አመራሮች በቀውስ ጊዜ ትምህርትን በሚመራበት ሁኔታና 2013 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኮረ በደሴና በደብረብርሃን ከተሞች በ2 ዙር የተሰጠው ስልጠና ተጠናቋል.።
ስልጠናውን መነሻ በማድረግም ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
የትምህርት አመራሮች ስልጠናው ወቅቱን የጠበቀና ተጨማሪ አቅም ፈጥሮልናል ብለዋል።
በኮቪድ19፣በአንበጣ፣በጉርፍመጥለቅለቅ፣በመፈናቀልና በወቅታዊ የሀገራችን የፀጥታ ችግር ትምህርት ቤቶችን መምራት ከባድቢሆንም ከመምህራንና ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ትምህርት ቤቶችን በመልካም ሁኔታ መምራት መቻሉ ተነግሯል።
መምህራን ከምንጊዜም በላይ መስዋት የከፈሉበት የትምህርት ዘመን ነው ያሉት የትምህርት አመራሮች መምህራን እውቀታቸውን፣ጊዜአቸውን፣ገንዘባቸውንና ደማቸውን ጭምር በመለገስ የሀገር ገንቢነታቸውን እየተወጡ ያሉ መሆናቸውን ነው በውይይቱ የተገለፀው።
በቀጣይም ከህብረተቡና ከመምህራን ጋር በመቀናጀት የመማር ማስተማሩን ሂደት ውጤታማ እንዲሆን ከምጊዜውም በላይ ወቅቱን ያገናዘበና በጥበብ መምራት ይገባል ተብሏል።
መንግስት ለመምህራን በየጊዜው የሚገባውን ቃል አለመመፈፀም ችግር ሊስተካከል ይገባል ያሉት አመራሮች የመምህራን ጅኤጅ የ9 ወር ክፍያ እና የተማሪዎች ማስክ ለብአትነት ተነስቷል።
ከመንግስት የሚጠበቁ የመፀሀፍትና ሌሉች የትምህርት ግብአቶች በፍጥነት ሊሟላ ይገባል ትብሏል።
መድረኩ ከሌሉች ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ የተጋራንበት ነብር ያሉት የትምህርት አመራሮች በቀጣይ ተሞክሮዎችን ይዘው በትምህር ቤታቸው የተሻለ ስራ ለመስራት እንደሚያግዛቸው ገልፀዋል።
በሁለቱም መድረኮች የተገኙት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈራ ፈይሳ መምህራንና የትምህርት አመራሩ ይህን አስቸጋሪ ጊዜ ለማለፍ የከፈሉትን መስዋትነት አመስግነው ይህንን አስቸጋሪ የቀውስ ጊዜ ግምት ውስጥ ያስገባ የትምህርት ቤት አመራር መፍጠር ይገባል ብለዋል።
በኮቪ 19 ምክንያት በርካታ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ትምህርት ቤት አለመምጣት ችግር በርብርብ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
ህብረሰቡን በማስተባበር የተጀመረውን የትምህርት ቤት ገጽታ ግንባታ በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ተብሏ።
በትምህርት ቤቶች ያለው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሰራ ስምምነት ተደርሷል።
