ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ሀላፊው አቶ አበባው ታደሰ እንደገለፁት በደሴ ከተማ የስልክ አምባ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ አስር የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ አምስት ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገበት ሲሆን በሁለት ፈረቃ አንድ ሺ በላይ ተማሪዎችን ያስተናግዳል፡፡
የመማሪያ ክፍል ግንባታው የአማራ ልማት ማህበር በስትራተጅያዊ የለውጥ ዕቅዱ ውስጥ በ2013 በጀት አመት ደረጃቸውን የጠበቁ 6 ሺ 020 መማሪያ ክፍሎችን የመገንባት ዕቅዱ አካል መሆኑንም አቶ አበባው ጠቅሰዋል፡፡
በያዝነው በጀት አመት ደሴና አካባቢው ማስተባበሪያ 376 ሚሊየን ብር የልማት ሀብት ለመሰብሰብ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን እስከ አሁን ጊዜ ድረስ የ2013 በጀት አመት 7 ሚሊዮን አንድ መቶ ሺ ብር የልማት ሀብት መሰብሰቡን ገልጧል፡፡
መረጃው የአልማ የፌስ ቡክ ገፅ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *