ለ ኦ ክፍል አመራሮች የማማከርና ሱፐርቪዘዥን ስልጠና ከህዳር 19-23/2013 ዓ.ም ድረስ በደሴ፣ ደብረ ታቦርና ደብረ ማርቆስ ከተሞች ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናዉን አስመልክቶ አስተያዬታቸዉን ከሰጡት ሰልጣኞች መካከል ወ/ሮ ስንቄ ከፈለኝ ስለቀዳማይ የልጅነት ዘመን እድገትና የትምህርት ዝግጅት መሰረታዊ እዉቀት እንዳገኙበትና ለኦ ክፍል የተዘጋጀዉን ስርዓተ ትምህርት በአግባቡ እንደተረዱ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም በሚደግፏቸዉ ትምህርት ቤቶች ህጻናት ጥሩ እሴት ተላብሰዉ በመልካም ስነ ምግባር እንዲቀረጹ ለማስቻል እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

ሌላኛዉ ሰልጣኝ አቶ ሷሊህ መሃመድ በበኩላቸዉ በስልጠናዉ የትምህርት ቤት እቅድ የማዘጋጀትና የመደገፍ ክህሎታቸዉን ከማዳበሩ ባሻገር ስለ ህጻናት እድገት ጥሩ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸዉ ገልጸዋል፡፡ በተለይ ደግሞ ስልጠናዉ የአመቱ ትምህርት የተጀመረበት ወቅት ላይ በመሰጠቱ ያገኙትን እዉቀትና ክህሎት በትክክል ለመተግበር እንደሚያስችላቸዉ አቶ ሷሊህ ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *