በአማራ ክልል የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከታህሳስ 12-14/2013 ዓ.ም በክልሉ በ5162 ት/ቤቶች እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
በክልላዊ ፈተና በመደበኛ፣በግልና በማታ የትምህርት ፕሮግራሞች ከ4መቶ 15 ሽህ በላይ ተማሪዎች ክልላዊ ፈተናውን የሚወስዱ ሲሆን ፈተናውን በውጤታማነት ለማጠናቀቅ በየደረጃው ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲከወኑ ቆይተዋል፡፡
በኮቪድ ምክኒያት የተቋረጠውን ትምህርት ተማሪዎች የማካካሻ ትምህርት በመስጠትና በሰነልቦና እንዲዘጋጁ ሲሰራ መቆቱ ከቢሮው ፈተና ክፍል የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡
ፈተናውን ለመስጠት ልዩ ልዩ የፈተና ቁሳቁሶች ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን የፈተና ሂደቱን ሊያስተባብሩ የሚችሉ አካላትንም የመምረጥ ስራ ተሰርቷል፡፡
ለሁሉም የወረዳ የፈተና ክፍል ባለሙያዎች ከሰሞኑ ኦሬንቴሽን በቢሮው በኩል የተሰጠ ሲሆን ተመሳሳይ ኦሬንቴሽን ለሚመለከታቸው አካላት በየደረጃው እየተሰጠ ነው፡፡ ባለፉት አመታት የታዩ አንዳንድ የፈተና ሂደት ክፍተቶች እንዳይደገሙ በቂ ዝግጅት መደረጉ ነው የተገለፀው፡፡
ወላጆችና ማህበረሰቡ ተፈታኝ ተማሪዎች በቂ የስነልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡ ፈተናው በመጭው ሰኞ ከታህሳስ 12-14/2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የወጣው መርሃ ግብር ያመለክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *