*ሰብአዊ ግብአት ማሟላት

  1. 142 የመጀመሪያና 54 የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ር/መምህራን ፣ 42 የመጀመሪያና 7 የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሱፐርቫይዘሮች ተመድበዋል

2.የ2,066 የዲፕሎማ፣ 454 የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው መምህራን ቅጥርና ስምሪት ተካሂዷል

  1. 2,937 በጎ ፈቃደኛ የዩኒቨርቲና የኮሌጅ ተማሪዎች በክረምት ወቅት ለ4,418 የመጀመሪያና 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ተሰጥቷል

*መሠረተ ልማት ማሟላት

  1. 56 አዲስ የመጀመሪያ ደረጃ እና 23 አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተከፍተዋል፡፡
  2. 768 ነባር የመጀመሪያና 138 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ደረጃ አሣድገዋል፡፡
  3. 2,551 የመጀመሪያና 597 ሁለተኛ ደረጃ መጨናነቅ ባለባቸው ትምህርት ቤቶች ተጨማሪ ክፍሎች ተገንብተዋል፡፡
  4. 1,327 የመጀመሪያና 36 የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መማሪያ ክፍሎችን መልሶ በአዲስ የመተካት ስራ ተሰርቷል

* የትምህርት መሣሪያዎችን ማሟላት በተመለከተ

  1. 1,975,940 የመጀመሪያና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪ መማሪያ መፃህፍት በአማርኛና በአፍ መፍቻ ቋንቋዎች ከ96 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ ማሳተምና ማሰራጨት ተችሏል።
  2. ለ114 ፕላዝማ ጥገና በማድረግ ለመማር ማስተር ዝግጁ የማድረግ ስራ ተሰርቷል
  3. 3,506 ጥቁር ሠሌዳና 32,989ኮምባይንድ ዴስክ ግዥ ተፈፁሞ የተሰራጨ ሲሆን 21,471 ጥቁር ሠሌዳና 69,659 ኮምባይንድ ዴስክ ጥገና ተደርጓል፣

4.በትምህርት ቢሮው በተመደበ በጀት 5836 ኮምባይድ ዴስክ እና ከፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር በተመደበ 185 ሚሊየን ብር ተጨማሪ ኮምባይድ ዴስኮች እየተመረቱ ነው

*የትምህርት ፋይናንስ ከማሟላት አንፃር

1.የተማሪ የድጎማ በጀት 291.99 ሚሊዩን ብር፣

2.የነፍስ ወከፍ በጀት 59.58 ሚሊዩን ብር፣

  1. የት/ቤቶች የውስጥ ገቢ 164.81 ሚሊዩን ብርና
  2. በህብረተሰብ ተሣትፎ 627.39 ሚሊዬን ብር ማሟላት ተችሏል፣

በአጠቃላይ በ6 ወራት በክልል ደረጃ የሚቀርቡ የሰብአዊ፣ የቁሣቁስና የፋይናንስ ግብአቶችን በማቅረብ በተለይም የመጽሀፍት አቅርቦትና ስርጭትን ችግር መፍታት በኩል የተሻለ ሥራ ተሠርቷል፡፡

በወረዳና በት/ቤት ደረጃ በየደረጃው ግብአቶችን ለማሟላት ከመንግሥት ከሚመደበው በጀት ጎን ለጎን ህብረተቡን በማሣተፍ የተደረጉ ጥረቶች መሻሻልን አሳይቷል፡፡

በአማራ ክልል የትምህርት ሥርዓቱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለመደገፍ ምን ተሰራ

@ በከልሉ ከሚገኙት 568 የመንግስት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 285 ትምህርት ቤቶች የኢንተርኔት መሰረተልማት ተጠቃሚ ሲሆኑ

* 183ቱ ትምህርት ቤቶች የብሮድባንድ ኢንተርኔት ጠቃሚ ናቸው፡፡

* 102 ትም/ቤቶች ደግሞ የቪሳት ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ሆነዋል።፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ግምግማ በደሴ ከተማ እንደቀጠለ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *