በሰሜን ወሎ ዞን ከ92 ሚሊዬን ብር በላይ በሆነ ወጭ የትምህርት ቤቶችን ገጽታ ለመቀየር እየተሰራ ነዉ፡፡
በዞኑ በመንግስት፣ በህብረተሰብ ተሳትፎ፣ በአልማና በጎ አድራጊ ድርጅቶችና ግለሰቦች አማካኝነት 92.4 ሚለዬን ብር በሆነ ወጭ የትምህርት ቤቶችን ገጽታ ለመቀየር እየተሰራ ነዉ፡፡ የሰሜን ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ የኋላእሸት ልዑልሰገድ እንደገለጸት በ68 ትምህርት ቤቶች የገጽታ ግንባታ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
በ16 ትምህርት ቤቶች የተከናወነዉ የገጽታ ግንባታ ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪዎቹ ግንባታዎች በመከናዎን ላይ መሆናቸዉን መምሪያ ኃላፊዉ አስረድተዋል፡፡ በአምስት ወረዳዎች ሰባት ትምህርት ቤቶች በሰቆጣ ቃል ኪዳን ስምምነት አማካኝነት እየተገነቡ የሚገኙ ናቸዉ፡፡
በሌላ በኩል በዞኑ በሚገኙ በሰባት መቶ ትምህርት ቤቶች ዉስጥ ባለፈዉ አመት ከተተከሉ 321 ሽህ በላይ ችግኞች በተጨማሪ በዚህ ክረምት ከ 156 ሽህ በላይ ችግኞችን ለመትከል የችግኝ መትከያ ጉድጓዶች ዝግጅት መደረጉን አቶ የኋላእሸት ልዑልሰገድ አክለዉ ገልጸዋል፡፡
እንደ መምሪያ ኃላፊዉ ገለጻ በዞኑ 150 በጎ ፈቃደኛ መምህራን በተለያዩ አካባቢዎች ህብረተሰቡ ከኮሮና ቫይረስ ራሱን እንዲጠብቅ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን በመስራት ላይ ሲሆኑ በዞኑ ከሚገኙ የትምህርት ተቋማትና በጎ ፈቃደኛ ሰራተኞች ለኮሮና መከላከል አግልግሎት የሚዉል 314, 387 ብር ተሰብስቧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዞኑ 58 ትምህርት ቤቶች ለለይቶ ማቆያነት ተለይተዉ አስፈላጊዉን ግብዓት ለማሟላት አየተሰራ ነዉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *