የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ዓመታዊ ዝውውር በየዓመቱ የዝውውር መመሪያውን መሰረት አድርጎ ሲካሄድ መቆቱ ይታወሳል፡፡ ባለፈው ዓመት በኮቪድ-19 ምክኒያት ያልተሰራው የመምህራንና የትምህርት ዓመራሮች ዝውውር በ2013 የትምህርት ዘመን የክልልና የ15 ዞን መምህራን ልማትና የመምህራን ማህበር ተወካዮች በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
ከዞን ዞን የሚካሄደው ዝውውር የመጀመሪያና 2ኛ ዲግሪ መምህራን እና አመራሮች እንዲሁም የመጀመሪያ ደረጃ የሊኒየርና ክላስተር የዲፕሎማ መምህራንና አመራሮች ያካተተ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
የትምህርት ደረጃንና ትምህርት አይነትን መሰረት አድርጎ ሚካሄደው የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ዝውውር አገልግሎት 80%፣ ጋብቻ10% ለተሿሚ ወይም ተመራጭ ደግሞ 10% ነጥብ ይሰጣል፡፡
በአማራ ክልል በመጀመሪያ ዲግሪ 7720 በ2ኛ ዲግሪ ደግሞ 837 መምህራን ዝውውር የሞሉ ሲሆን በዲፕሎማ ሊኒየር 8388 በክላስተር ደግሞ 5450 መምህራን ዝውውር ሞልተዋል፡፡
በተመሳሳይ 847 የመጀመሪያ ደረጃ እና 50 የ2ኛ ደረጃ የትምህርት አመራሮች ዝውውር መሙላታቸው ታውቋል፡፡
ዝውውሩ በቀጣይ ሳምንት ተጠናቆ ለዞኖች እንደሚላክ ይጠበቃል፡፡ መረጃውን በገፃችን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡