በሰሜን ወሎ ዞን ሐብሩ ወረዳ የምትገኘው የመሃል አንባ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤትን ምቹ ሳቢና ማረኪ ለማድረግ ከአጋር አካላት ጋር እየተሰራ ነው።
በትምህርት ቤቱ ራሱን የቻለና ደረጃውን የጠበቀ የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች ግቢ ወርልድ ቪዥን በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ተገንብቶ በመጠናቀቅ ላይ ነው። በሌላ በኩል ለትምህርት ቤቱ ቤተ መጽሃፍትና የቤተ ሙከራ ክፍሎችን በህብረተሰቡና በወረዳው ትብብር ለማስገንባት በሂደት ላይ እንደሚገኝ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ዋሲሁን አየሁ ገልጸውልናል። ትምህርት ቤቱ ዋና ዋና የሚባሉ የትምህርት ቤቱን የግንባታ እጥረቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ገንብቶ ለማጠናቀቅ እየሰራ እንደሚገኝ ርዕሰ መምህሩ አክለው ገልጸዋል።
በሌላ በኩል የትምህርት ቤቱን ቅጥር ግቢ አረንጓዴ ለማድረግ ባለፈው አመት ከተተክሉት ሁለት ሽህ ችግኞች በተጨማሪ በዚህ አመት ከሰባት ሽህ በላይ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ለመትክል በትምህርት ቤቱ የችግኝ መትከያ ጉድጓድ ዝግጅት እየተደረገ ነው።
የመሃል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጭ በመሆናቸው በቤታቸው ሆነው ትምህርታቸውን መከታተል እንዲችሁ በመምህራን የተዘጋጁ የጥያቄ ወረቀቶችንና ማስታወሻዎችን አዘጋጅቶ ለተማሪዎች እያደረሰ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *