የበጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ አለም አቀፍ ወረርሽን የሆነውን ኮሮናን ለመከላከል ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ነው።
የበጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የህብረተሰቡ እራሱን ከኮሮና( ኮቪድ 19) እንዲጠብቅ በደቡብ ጎንደር ዞን በሚገኙ ወረዳዎች እየተንቀሳቀሰ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችን በመስጠት ላይ መሆኑን የኮሌጁ ዲን አቶ ማስተዋል አሰሙ ገልጸውልናል።
በሌላ በኩል የበጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለዞኑ የኮሮና መከላከል ግብረ ሃይል የአንድ መቶ ሽህ ብር ድጋፍ ማድረጉን ዲኑ ተናግረዋል።
ኮሌጁ ለኮቪድ 19 ታማሚዎች የህክምና ማዕከል ሆኖ በመመረጡ የውሃ የሻወርና ሽንት ቤት ግባአቶችንም በማሟላት ላይ ይገኛል።
ኮሌጆች ካሏቸው ሶስት አላማዎች መካከል የመማር ማስተማር፣ ማህበራዊ አገልግሎት መስጠትና ጥናት ምርምር ማካሄድ ናቸው። በመሆኑም የበጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በዚህ አስቼጋሪ ወቅት ሳኒታይዘር አምርቶ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በመስራት ላይ መሆኑ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግና ኮሌጁንም ለህክምና ማዕከል በማዘጋጀት ተልዕኮውን እየተወጣ እንደሚገኝ የኮላጁ ዲን አቶ ማስተዋል አሰሙ ነግረውናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *