covid-19
“ማስክ – አማራ” ሕዝብን የማዳን ዘመቻ!
በሚል መሪ መልዕክት ከዛሬ ነሐሴ 22 እስከ 30 ይካሄዳል።
ዘመቻው የሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በመሆኑ ለራስ ደህንነት ኃላፊነት መውሰድ ይገባል። ስለሆነም ማስክ በመጠቀም የኮሮና ቫይረስን የመከላከል ግዴታዎን ይወጡ።
?ከዛሬ አርብ ጀምሮ፦
?ከክልል ቢሮዎች እስከ ወረዳ ኃላፊዎችና ሁሉም ባለሙያዎች ማስክ ሳይለብሱ ወደ ቢሮ መግባት ክልክል ነው።
? ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ማስክ ሳያደርግ እንዳይንቀሳቀስ በትኩረት እንስራ፣እንገንዘብ፣እናስገንዝብ።
ነገን ብሩህ ለማድረግ፦
አካላዊ ርቀታችንን በመጠበቅ፣
አዘውትረን እጆቻችንን በመታጠብ፣
የፊት ጭምብልን በአግባቡ በመጠቀም፣
ከህክምና ባለሙያዎች የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በመተግበር ከኮሮና ወረርሽኝ ራሣችንን እንታደግ!
ነገን ለመኖር ዛሬን እንጠንቀቅ!
መረጃው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *