“መምህራን የአለም ብርሃን” በብዙዎች ዘንድ የሚነገር ትክክለኛና ዘመን የማይሽረው ቃል ነው፡፡
መምህርነት ራስን እንደሻማ እያቀለጡ ለሌሎች መብራት መሆን ነው፡፡ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሀገራችን በተከሰተ ማግስት ከባድ ተፅዕኖ ያሳደረው በትምህርት ዘርፉ ላይ ነው፡፡ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፡፡ ተማሪዎች ከወላጆቻቸው ጋር ሆነው ከ 7ወር በላይ ከትምህርት ገበታ ርቀዋል፡፡ ይህንን አስቸጋሪ ወቅት ለማለፍ የትምህርት ቤቶችን መልሶ መክፈት የተመለከቱ ስታንዳርዶች መውጣታቸው ይታወቃል፡፡ ከነዚህ መካከል ሁሉም ተማሪዎች አፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እንዲለብሱ፣ በአንድ ክፍል 30 ተማሪዎች ብቻ ሆነው እንዲማሩ፣ ተማሪዎች ርቀታቸውን እንዲጠብቁ፣ በትምህርት ቤቶች የእጅ ንፅህና መጠበቂያ ውሃና ሳሙና እንዲዘጋጁ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
በየደረጃው የተቋቋመው ግብረ ሃይል እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ያደረገው ጥረት አበረታች ቢሆንም በመምህራን ዘንድ የተስተዋለው ተነሳሽነትና የአርበኝነት ስሜት ግን ታሪክ ሲዘክረው የሚኖር ሆኖ የሚመዘገብ ነው፡፡ በክልላችን ሁሉም ትምህርት ቤቶች የመምህራን ተነሳሽነትና ትጋት ቢያስደስተንም በምዕራብ በለሳ ወረዳ ድርቃ እና መንቲ መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የሂሳብና እንግሊዘኛ መምህራን ሙሉ 60 ክፍለ ጊዜ፣ በአርባያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የኢኮኖሚክስ መምህራን 42 ክፍለጊዜ ይዘው ተማሪዎችን ለመርዳት እያደረጉት ያለውን አርአያነት ያለው ስራ የሙያውን ክብር ከፍ የሚያደርጉና የሚያስመሰግኑ ናቸው፡፡ በዚህም የአብክመ ትምህርት ቢሮ ላቅ ያለ ክብርና ምስጋና እያቀረበ ውድ የዚህ ፌስ ቡክ ተከታዮቻችንም መምህራንን ታከብሩልን ዘንድ እንጠይቃለን!!
ክብርና ሞገስ የሰውን ልጅ አዕምሮ ለሚያንፁ መምህራን!!
