የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የ8ኛ ክፍል ፈተናን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በዚህም መሰረት የ8ኛ ክፍል ፈተና ከታህሳስ 12-14/2013ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ቢሮ ሃላፊው ተናግረዋል፡፡ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተናን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር በሚያወጣው ፕሮግራም መሰረት የሚፈጸም ይሆናል ተብሏል፡፡
ዞንና ወረዳዎችም ይህንን ተገንዝበው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ሲያደርጉ እንዲቆዩ ቢሮ ሃላፊው አሳስበዋል፡፡
ለ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የማካካሻ ፕሮግራሞች ተዘጋጅተው ሲሰጡ መቆየቱን የገለጹት ሃላፊው ተማሪዎችም ያለምንም ጭንቀት በቀሪ ቀናት የቀራቸውን ይዘቶች በመከለስ ለፈተና እንዲዘጋጁ ዶ/ር ይልቃል ከፋለ አሳስበዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን https://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን!!

See Less

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *