ወረዳው ለትምህርት ጥራት ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን መጠበቅ አንዱ መስፈርት እንደሆነ በማመን ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ በርካታ የሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤቶችን እያስገነባ ይገኛል፡፡ የዚህ ትምህርት ቤት መሰረተ ድንጋይ መጣል ለአከባቢው ህብረተሰብ ለዘመናት የትምህርት ቤት ይገንባልኝ ጥያቄን እንደሚመልስ በዕለቱ ያነጋገርናቸው የአከባቢው ማህበረሰቦች ተናግረዋል፡፡
ወረዳው በ2012 በአንድ አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አንድ የሁለተኛ ደረጃ አስገንብቶ ለትምህርት ማቅረቡን ያስታወሱት አስተያየት ሰጪዎች በዚህ አመት ደግሞ ሌላ ለመስራት መዘጋጀቱ ወረዳው ለልማት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
በዕለቱ የእንኳን ደስ አላችሁ ንግግር ያደረጉት የጎዛምን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገደፋው ይርሳው እንደገለፁት ይህ ትምህርት ቤት በዋናነት በአልማ የሚገነባ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን ነገርግን አልማ ብቻዉን ሊያሳካዉ ስለማይችል የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነዉ ብለዋል ።
መንግስት የህዝቡን መሰረታዊ የልማት ጥያቄ ደረጃ በደረጃ ለመመለስ እንደሚሰራ ገልፀው ይህ የመሰረት ድንጋይ የዚህ ሂደት አካል ነው ብለዋል፡፡
ዋና አስተዳዳሪው ስግብግቡ ጁንታ የብልፅግና ጉዞአችንን ለማደናቀፍ በርካታ እንቅፋቶችን እየፈጠረብን ቢሆንም ይህን አስቸጋሪ ጊዜ በድል በመሻገር የብልፅግና ጉዞአችንን እንሳቀጥላለን ብለዋል፡፡ አቶ ገደፋው አክለው እንደገለፁት በዚህ ፕሮጀክት የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ስራ ፈጣሪ ወጣቶች በወረዳችን ለማብዛት ይቻል ዘንድ ወጣቶችን ታሳቢ ተደርጎ እንደሚሰራ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
የጎዛምን ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ነግሬዉ በበኩላቸው በክልላችን ብሎም በወረዳችን ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች አነስተኛ እንደሆኑ ገልፀው ይህንን ችግር ከአልማ ጋር በመተባበር እየፈታን እንገኛለን ብለዋል፡፡
ኃላፊው እንደገለፁት ካለፈው አመት ጀምሮ በትምህርት ዙሪያ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ገልፀው በቀጣይም የተጀማማሩ ስራዎችን በማጠናቀቅ አሁን የምንጀምራቸውን የልማት ስራዎች በተያዘላቸው ጊዜ አጠናቀን ለአገልግሎት ዝግጁ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
በመጨረሻም አቶ ገደፋዉ፣ አቶ ገብሩና የአልማ ተወካይ አቶ ያለዉ የመሰረት ድንጋዩን አስቀምጠዋል ።
ዘገባው የጎዛመን ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *