ስልጠናው ትኩረት ያደረገው በሥነ-ምግባር ፅንሠ ሃሳብ፣አስፈላጊነት እና በአጠቃላይ ትም/ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍታሃዊነት ዙሪያ ሲሆን ስልጠናውንም የዞንና ወረዳ የስርዓተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪወች ተሳትፈውበታል።
በስልጠናው ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የቢሮው ም/ሃላፊ አቶ መኳንት አደመ እንደተናገሩት ከአጋር ድርጅቶች፣ ህብረተሰቡና መንግሰት የሚመደቡትን በጀት ለታለመለት አላማ በማዋል የመማር ማስተማሩን ሂደት በውጤታማነት መምራትና በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ብለዋል።
በትምህርት ቤቶች ያለውን ውስን ሀብት ከሙስና የፀዳ አሰራር በመተግበር ር/መምህራንና ሱፐር ቫይዘሮች መስራት አለባቸው ያሉት ሃላፊው የትምህርትን ጥራት በተገቢው መንገድ ማረጋገጥ እንደሚገባም አሳስበዋል።
ስልጠናው የሚሰጡት የቢሮው የስነ ምግባር መኮነን አቶ ጉባይ ከልካይም የስልጠናው አላማ በትምህርት ቤቶች የሚስተዋለውን የሀብት ብክነት ለማስቀረት እና ስለ ሙስናና ስነ ምግባር ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሆነ አስረድተዋል።