የብቃት ፈተናውን የሚወስዱት በአማራ ክልል በሚገኙ አስር መምህራን ትምህርት ኮሌጆች በተለያዩ የትምህርት ምስኮች በግልና በመንግስት ሲሰለጥኑ የቆዩ 12,950 ተመራቂ የዲፕሎማ እጩ መምህራን መሆናቸዉን በትምህርት ቢሮ የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ይገርማል አያሌዉ ተናግረዋል፡፡
ፈተናው በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በአዊኛ፣ በኽምጣና በኦሮምኛ በጥቅሉ በአምስት ቋንቋዎች በአስሩም የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች ህዳር 30/2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ አቶ ይገርማል አያሌው አክለው ገልጸዋል፡፡
የብቃት ፈተናውን የሚወስዱት በ2012 የትምህርት ዘመን መመረቅ የነበረባቸው ቢሆንም ኮቪድ 19 በትምህርት ስርዓቱ ባሳደረው ተጽኖ ምክንያት በዚህ አመት የማካካሻ ትምህርት ወስደው ለመመረቅ በዝግጅት ላይ ያሉ ተመራቂ የዲፕሎማ እጩ መምህራን መሆናቸዉ ታውቋል፡፡
