በአለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የገጽ ለገጽ ትምህርት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን በአሁን ሰዓት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የመማር ማስተማር ስራው የተጀመረ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡
በዚሁ መሰረት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለመከለስ የሚያስችል የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች በሰባት የትምህርት አይነቶች ማለትም እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስ ተዘጋጅቶ በኢትዮጵያ ትምህርት በቴሌቪዥን ጣቢያ (MOE-TV) ከሰኞ እስከ እሁድ በድግግሞሽ የሚተላለፍ ስለሆነ መከታተል የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የተማሪዎች ወላጆችም አስፈላጊውን ድጋፍ ለልጆቻችሁ እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡
moe

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *