አለም አቀፍ ወረርሽኝ በሆነዉ ኮቪድ 19 እና በወቅታዊ የፀጥታ ችግር የተራዘመው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በአማራ ክልል በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች እየተሰጠ እየተሰጠ ነዉ፡፡
ተዘዋውረን በተመለከትናቸዉ የባህርዳር ከተማ የፈተና ጣቢያዎች ተማሪዎች በተረጋጋ መንፈስ በመፈተን ላይ ናቸዉ፡፡
የእውቀት ፋና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ም/ርዕሰ መምህር ወ/ሮ አበባ ሽፈራው በትምህርት ቤቱ ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራ የሰራን በመሆኑ ለተማሪዎችም በቂ ኦሬንተሸን በመሰጠቱ የጥዋቱን መርሀ ግብር ሁሉም ተማሪዎች ቀድመው በመገኘታቸው ፈተናው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ የፈተና ጣቢያ ኃላፊው አቶ ጌታቸው ፈቃዱ ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት የፈተናዎች ደህንነት ተጠብቆ ትምህርት ቤት ማድረስና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በአግባቡ በመከወናቸው ፈተናው በጥሩ ሁኔታ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡
የጠዋቱን መርሀ ግብር አጠናቀው ሲወጡ ያገኘናቸው የእሸት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተፈታኝ ተማሪ ሀይለሚካኤል ማንደፍሮና ህሊና ቴዎድሮስ ፈተናው በኮቪድና በወቅታዊ ችግር ምክንያት ቢዘገይም በተሰጠን የማካካሻ ትምህርት፣ የመምህራን ምክርና የወላጆች ድጋፍ በመታገዝ ባደረግነው ሰፊ ዝግጅት ፈተናው ጥሩ መሆኑን ነግረውናል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የስርአተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ካሴ አባተ ለፈተናው በተደረገው የቅድመ ዝግጅት ስራ በክልሉ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ፈተናው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *