የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከትምህርት አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር ለ2 ቀናት በደሴ ከተማ ሲያካሂደው የቆየውን የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አጠናቋል።

በእቅድ አፈፃፀም ግምገማው ባለፉት 6 ወራት ኮሮናን እየተከላከልን እንማር እየተማርን ኮሮናን እንከላከል በሚል መሪ መልዕክት የተጀመረውን የዘመኑን የመማር ማስተማር ሂደት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተነግሯል።

በተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች ውስጥ ሆነን ያሳለፍነውን የግማሽ አመት የትምህርት ዘመን በርካታ መልካም ተግባራት የተከወኑ ሲሆን ችግሮች እንደነበሩም በውይይቱ ተነስቷል።

ከመልካም ተግባራት በመማርና ከችግሮች ትምህርት በመውሰድ የትምህርት ዘመኑን በውጤታማነት ለማጠናቀቅ በትኩረት መስራት ይገባል ተብሏል።

በመድረኩ በ6 ወራት እቅድ አፈፃፀምን ጨምሮ በሌሉች ርዕሰ ጉዳዮች ዉይይት ከተደረገ በኃል ቀጣይ አቅጣጫዎች የተቀመጡ ሲሆን በተለይ በትምህርት ገበታ ያሉ ተማሪዎች ትምህርት እንዳያቋርጡ በትኩረት መስራት፣የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ ማድረግ፣ የትምህርት ቤቶችን ገፁታ ለማሻሻል ከአልማና አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ መስራት፣ የትምህርት ጊዜው አጭር በመሆኑ የማካካሻ ትምህርት በመስጠት ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የተጀመረውን መልካም ስራ አጠናክሮ መቀጠል በሚሉትና በሌሉቹ ዝርዝር ተግባራት ዙሪያ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ይልቃል ከፋለ (ዶክተር) በሰጡት ቀጣይ አቅጣጫ መድረኩ ተጠናቋ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *